ወልዋሎዎች የመሀል ተከላካይ አስፈረሙ

ወልዋሎዎች የመሀል ተከላካይ አስፈረሙ

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበረው ተከላካይ ወደ ቢጫዎቹ አምርቷል

በዝውውር መስኮቱ አስራ አንድ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸውን በመቀላቀል ለ2018 የውድድር ዓመት በዝግጅት ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮ ኤሌክትሪል ቆይታ የነበረውን የመሀል ተከላካይ አስፈርመዋል። ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች በእግር ኳስ ሂወቱ ወልቂጤ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ስያድጉ ጉልህ አስተዋፅዖ ያበረከተው ጌታሁን ባፋ ነው።

ቡድኑን በአምበልነት በመራበት የ2017 የውድድር ዓመት በ25 ጨዋታዎች ተሰልፎ 2225′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው የመሀል ተከላካዩ ከዚህ ቀደም
በነቀምት ከተማ፣ ደቡብ ፓሊስ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከተጫወተ በኋላ መዳረሻው ወልዋሎ በማድረግ በአሁኑ ሰዓት ከስብስቡ ጋር ተቀላቅሎ ወደ መቐለ ከተማ ጉዞ ጀምሯል።

ከወልዋሎ ጋር በተያያዘ ሌላ ዜና ላለፉት ሳምንታት በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በማከናወን ላይ የቆየው ቡድኑ በመስቀል ዓጋመ ዋንጫ ለመሳተፍ ወደ ዓድ ግራት ከተማ በማምራት ላይ ይገኛል።