መቐለ 70 እንደርታ የሁለት ተጫዋቾች ዝውውር አገባዷል
በመጀመርያው ሳምንት በሽረ ምድረ ገነት ሽንፈት የገጠማቸውና በሁለተኛው የጨዋታ ሳምንት በነገው ዕለት መቻልን የሚገጥሙት በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት የሚመሩት መቐለ 70 እንደርታዎች የሁለት ተጫዋቾች ዝውውር አጠናቀዋል፤ ቡድኑን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ደግሞ ተመስገን ተስፋዬ እና ብሩክ ቃልቦሬ ናቸው።
በተከላካይ እና በአማካይነት መጫወት የሚችለው ተመስገን ተስፋዬ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መድን፣ ሻሸመኔ ከተማ እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ የሊጉን ዋንጫ ካሳካበት ቡድን ጋር የነበረውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ማረፍያው መቐለ 70 እንደርታ ሆኗል። ከዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ የተመለሰው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ወላይታ ድቻ፣ ወልድያ ከተማ፤ አዳማ ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀምበሪቾ ተጫዋች ብሩክ ቃልቦሬ ደግሞ ሁለተኛው ወደ መቐለ 70 እንደርታ ያመራ ተጫዋች ሆኗል።