አፍቅሮት ሰለሞን ወደ ሽረ ምድረ ገነት አምርቷል

አፍቅሮት ሰለሞን ወደ ሽረ ምድረ ገነት አምርቷል

ባለፈው ዓመት ከዐፄዎቹ ጋር ቆይታ የነበረው ተጫዋች ሽረ ምድረገነትን ተቀላቀለ

በመጀመርያው ሳምንት ላይ በዳንኤል ዳርጌ ብቸኛ ግብ መቐለ 70 እንደርታን አንድ ለባዶ ያሸነፉት በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመሩት ሽረ ምድረገነቶች ከሳምንታት በፊት መቐለ 70 እንደርታን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው በመስመር አጥቂነት እንዲሁም በአማካይ ቦታ ላይ መጫወት የሚችለውን አፍቅሮት ሰለሞን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በተጠናቀቀው ዓመት በፋሲል ከነማ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ከደደቢት ታዳጊ ቡድን ከወጣ በኋላ በ2011 በፕሪምየር ሊጉ በ2012 ደግሞ በከፍተኛ ሊግ አሳዳጊ ክለቡን ያገለገለ ሲሆን ከዛ በኋላም በኢትዮጵያ መድን፣ ገላን ከተማ፣ ሀምበሪቾ እንዲሁም በፋሲል ከነማ መጫወት ችላል፤ አሁን ደግሞ ከቀድሞ አሰልጣኙ ዳንኤል ፀሐዬ ጋር በድጋሜ ለመስራት ወደ ሽረ ምድረ ገነት አምርቷል።