በአሰልጣኝ ራመቶ መሐመድ የሚመሩት ባቱ ከተማዎች 15 አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የ11 ተጫዋቾችን ውል አድሰዋል።
በጫላ አቤ
ለ2018 የኢትዮጵያ ክፍተኛ ሊግ በምድብ “ሀ” ሐዋሳ ከተማ የተመደቡት ባቱ ከተማዎች 15 አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና የ11 ተጫዋቾችን ውል በማደስ ቡድናቸውን አጠናክረዋል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለረዥም ዓመታትን መጫወት የቻለው ግብ ጠባቂው መሳይ አያኖ ፣ የፊት መስመር አጥቂ የሆነው እና ሻሸመኔ ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ባደገበት ዓመት የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የነበረው ያለፈው ዓመት በወራቤ ቤት ማሳለፍ የቻለው ፉዓድ መሐመድ ፣ የአክሱም ከተማ አማካዩ ክንዳለም ፍቃዱ ፣ በገላን ከተማ እና በሸገር ከተማ እንዲሁም ያለፈውን ዓመት በሻሸመኔ ከተማ የቀኝ መስመር ተመላላሽ ሆኖ የተጫወተው አረጋ ማሩ እንዲሁም ምስጋና አንጋሶ ከአምቦ ከተማ ፣ ጸጋአብ ወንዳየው ከደደቢት ፣ ብሩክ ወንዶ ከቤንች ማጂ ቡና ፣ አሸናፊ ካሳ ከሸገር ከተማ ፣ አመንቲ አቢቲ ከሸገር ከተማ ፣ አሸናፊ በቀለ ከነገሌ አርሲ ፣ ኪሩቤል አበበ ከቦዲቲ ከተማ ፣ እንደሻው ታምሬ ከአምቦ ከተማ ፣ ሳሙኤል ጃግሰው ከቦዲት ከተማ ፤ ናትናኤል ዘሪሁን ከኢትዮጵያ መድን ፣ እና ዮናታን አምባየ ከ እንጅባራ ከተማ ቡድኑን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾች ናቸው።

ከቡድኑ ጋር ለመቀጠል ውል ያደሱት የተከላካይ አማካዩ ጎሳ በሽር ፣ ግብ ጠባቂው ሀብትና ዓለሙ ፣ አማካዩ አብርሃም አልዲ ፣ ተከላካዩ ብርሃኑ ወልቄቶ ፣ አጥቂው አሚር ቸርነት ፣ የተከላካይ አማካዩ አቡበከር ኑሪ ፣ አማካዩ ተማም ከድር ፣ አጥቂው በረከት ራመቶ ፣ የግራ መስመር ተከላካዩ ጆንቴ ጋማቹ ፣ አማካዩ ዮሐንስ ሲማሙ ፣ አማካዩ መሐመድ ከድሮን ጨምሮ በአጠቃላይ ቡድኑ በ26 ተጫዋቾች መጠናከሩን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።


