በድሬዳዋ እና አበበ ቢቂላ ስታዲየሞች የሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ላይ ለውጥ ተደርጓል

በድሬዳዋ እና አበበ ቢቂላ ስታዲየሞች የሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ላይ ለውጥ ተደርጓል

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር ላይ የውድድር ስፍራ ለውጥ ተደርጓል።

ከሕዳር 6 እስከ 23 በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር ላይ የውድድር ስፍራ ለውጥ ተደርጓል። ቀድሞ በወጣው መርሐግብር መሰረት የምድብ ጨዋታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ቀጥለው የሚካሄዱ ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም እንዲካሄዱ ታስቦ የነበረ ቢሆንም አዲስ በወጣው መርሐግብር መሰረት የምድብ ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ እና ድሬዳዋ ስታዲየሞች ከተከናወኑ በኋላ እስከ ፍፃሜው ድረስ ያሉ መርሐግብሮች በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚከናወኑ ይሆናል።

አስር ሀገራት በሚሳተፉበት ውድድር በምድብ አንድ
ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ርዋንዳ ሲደለደሉ በምድብ ሁለት ዩጋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ቡሩንዲ ተደልድለዋል፤ ውድድሩም ከሁለት ቀናት በኋላ ሶማልያ እና ደቡብ ሱዳን በሚያደርጉት ጨዋታ ሲጀምር ሀገራችን ኢትዮጵያም ከርዋንዳ በምታደርገው ጨዋታ ውድድሯን ትጀምራለች።