ሽረ ምድረ ገነት ተከላካይ አስፈረመ

ሽረ ምድረ ገነት ተከላካይ አስፈረመ

ባለፉት ዓመታት በመቻል ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ሽረ አምርቷል

23 ነጥብ በመሰብሰብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው የመጀመሪያውን ዙር ያገባደዱት ሽረ ምድረ ገነቶች ባለፉት ዓመታት በመቻል ቆይታ የነበረው እና በቅርቡ ከጦሩ ጋር በስምምነት የተለያየውን የመሀል ተከላካዩ ደሳለኝ ከተማን አስፈርመዋል። በመሀል ተከላካይነት እንዲሁም በተከላካይ አማካይ ላይ መጫወት የሚችለው ይህ ተጫዋች ከዚህ ቀደም በመቻል እና በሰሜን ሸዋ ደ/ብርሀን መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በቅጣት የተመናመነውን የሽረ ምድረ ገነት የተከላካይ ክፍል ክፍተት ለመድፈን ወደ ክለቡ አምርቷል።