የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኢትዮጵያ መድን ተቀላቀለ

የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኢትዮጵያ መድን ተቀላቀለ

ባለፉት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ወጣት ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርቷል።


ቀደም ብለው ብሩንዳዊው አልፍሬድ ንኩሩንዚዛን የግላቸው ያደረጉት ኢትዮጵያ መድኖች አሁን ደግሞ ባለፉት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ወጣቱ የቀኝ መስመር ተከላካይ አማኑኤል ልዑል አስፈርመዋል።

ላለፈው አንድ ዓመት ከመንፈቅ በመቐለ 70 እንደርታ ዋናው ቡድን ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በአሳዳጊ ክለቡ ቀሪ የስድስት ወራት ውል ቢኖረውም አሁን ግን ከዓመታት በፊት ወደ መቐለ 70 እንደርታ ታዳጊ ቡድን ከቀላቀሉት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይለ ጋር በድጋሜ ለመስራት ኢትዮጵያ መድን ተቀላቅሏል።