የመስመር አጥቂው ማረፊያ ታውቋል

የመስመር አጥቂው ማረፊያ ታውቋል

ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የተለያየው ኪቲካ ጅማ ሌላኛውን የሊጉን ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል

የእግርኳስ ህይወቱን በኢትዮጵያ ቡና የጀመረው የመስመር አጥቂው ኪቲካ ጅማ በዘንድሮ የውድድር ዓመት መቐለ 70 እንድርታን በመቀላቀል ያለፉትን ስድስት ወር ቡድኑን ሲያገለግል መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ሆኖም ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከክለቡ ጋር በገባው እስጣገባ በትናንትናው ዕለት በፌዴሬሽኑ ውሳኔ አግኝቶ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል። ከመቐለ 70 እንደርታ መለያየቱን ተከትሎ ክለቦች ተጫዋቹን የማስፈርም ፍላጎት ቢያሳዩም ምርጫው ነጌሌ አርሲ መሆኑና ሂደቱ የቀረው ይፋዊ ፊርማ ብቻ መሆኑም ታውቋል።

በኢትዮጵያ ቡና ከተስፋ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ግልጋሎት የሰጠው ኪቲካ በገላን ከተማ ፣ በኢትዮጵያ መድን ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ ካነሳ በኋላ ያለፉትን ስድስት ወራት በመቐለ ሰባ እንድርታ ቆይታ አድርጎ አሁን መዳረሻው ነገሌ አርሲ ሆኗል።