ሪፖርት | በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

ሪፖርት | በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

የ22ኛ ሳምንት መዝጊያ ጨዋታ በሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ መካከል የተደረገ ሲሆን ጨዋታው 1-1 በሆነ በአቻ ውጤት ተቋጭቷል።

አዳማ ኬታማዎች በእግር ኳስ እንቅስቃሴ ብልጫ በወሰዱበት የመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ይህ ነው የሚባል የግብ ሙከራ ያላስመለከተን ሲሆን የሀድያ ሆሳዕና የጤና ባለሙያ ከዕለቱ ዋና ዳኛ ዳንኤል ግርማይ ጋር በፈጠሩት አለመግባባት በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱ መሰናበቱ አነጋጋሪ ክስተት ሆኗል።

ከእረፍት መልስ ሁለተኛው አጋማሽ ልክ እንደተጀመረ አዳማ ከተማዎች መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አስቆጥረዋል። 47ኛው ደቂቃ ላይ አህመድ ሁሴን በጥሩ ሁኔታ ወደ ሳጥን ይዞት የገባውን ኳስ በአስገራሚ ሁኔታ ሙሬት ለመሬት በመምታት ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።

ከግቡ መቆጠር በኋላ ሀድያ ሆሳናዎች ጫናቸውን ፈጥረው በመጫወት አቻ መሆን የቻሉበትን ግብ አስቆጥረዋል። በ61ኛው ደቂቃ ኢዮብ አለማየሁ ያቀበለውን ኳስ ተቀይሮ የገባው ታሪኩ ፀደቀ ወደ ሳጥን ወደ ሳጥን ይዞ በመግባት ግብ አስቆጥሮ ሀድያ ሆሳናን አቻ ማድረግ ችሏል።

ከግቦቹ መቆጠር በኋላ በአዳማ ከተማ በኩል አብዱልከሪም መሐመድ ከርቀት በሞከረው እና ኢላማውን ባልጠበቀው እንዲሁም በሀድያ ሆሳዕና በኩል ሱራፊል ተመስገን ተጫዋቾችን አልፎ የሞከረው ኳስ በግብ ጠባቂው የተመለሰባቸው እጅግ ለግብ የቀረቡ ነበሩ። ይህንንም ተከትሎ ጨዋታው ተጨማሪ ግቦችን ሳያስመለክተን 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።