ነገሌ አርሲ አጥቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

ነገሌ አርሲ አጥቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

በ 38 ነጥብ 3ኛ ደረጃ የተቀመጡትና ወደ ፕሪምየር ሊጉ ባደጉበት ዓመት ውጤታማ ጊዜ በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ነጌሌ አርሲዎች ናይጄርያዊ አጥቂ ንዲፍሬክ ኤፊዮንግ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ከዚህ ቀደም በሀገሩ ክለቦች አቢያ ዋርየርስ ፣ አክዋ ዩናይትድ እና ሪቨርስ ዩናይትድ እንዲሁም በሊብያው አል አህሊ፣ ኦሊምፒክ ሳፊ ፣ አል ቁዋ አል ጃው ፣ አል ናፍት፣ ኒውሮዝ  እና አል ሄዶድ መጫወት የቻለው ይህ የ27 ዓመት አጥቂ በ2016 በብራዚል በተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ላይ የነሐስ ሜዳሊያ ያሸነፈው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን አባል ሲሆን በ2021 ደግሞ ከአካዋ ዩናይትድ ጋር የናይጄሪያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፏል።

አስቀድመው የዝውውር መስኮቱ ሳይዘጋ በቅድመ ስምምነት ያመጡት አጥቂው ሰጎኖቹን በማጥቃቱ ረገድ ያለባቸውን ውስን ክፍተት ይቀርፋል ተብሎ ይታሰባል።