ቀይ ቀበሮዎቹ ዛሬ ተጋጣሚዎቻቸውን ያውቃሉ

ቀይ ቀበሮዎቹ ዛሬ ተጋጣሚዎቻቸውን ያውቃሉ

የቶታል ኢነርጂስ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ዛሬ ይፋ ይሆናል።

ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ያለፈው
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ  ተጋጣሚዎቹን ያውቃል።  የምድብ ድልድል ስነ ስርዓቱ ዛሬ በግብፅ መዲና ካይሮ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን የዕጣ አወጣጥ ሂደቱ ከመካሄዱ በፊትም ሁሉም ቡድኖች የተደለደሉበት ቋት አውቀዋል። በዚህ መሰረት ቻምፕዮኗ ሞሮኮ እና ማሊን ጨምሮ ሴኔጋል እና ኮትዲቯር በቋት 1 ፤ ቋት 2 ደቡብ አፍሪካ፣ ካሜሩን፣ አንጎላ እና ቱኒዚያ ፤ ቋት 3 ዩጋንዳ፣ ግብፅ፣ አልጄሪያ እና ታንዛኒያን የሚያካትት ሲሆን ቋት 4 ደግሞ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ሞዛምቢክን ያካተተ ሆኗል።