ከማላዊ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ልምምዱን አከናውኗል።

ግንቦት 29 እና ሰኔ 2 በድሬዳዋ ስታዲየም ከማላዊ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዚህ ሰዓት በንግድ ባንክ ሜዳ የመጀመሪያ ልምምዱን አድርጓል።
ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል 22 የቡድኑ ተጫዋቾች የተገኙ ሲሆን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ የ34ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን መሠረት በማድረግ ከተጠቀሰው ዝርዝር ላይ ለውጥ እንደሚኖር ቢገልፁም በመስመር አጥቂው መስፍን ታፈሰ ምትክም ሆነ ሌላ አዲስ ጥሪ የተደረገለት ተጫዋች የለም።
ለመጀመርያ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው ጀሚል ያዕቆብ፣ ፍፁም ፍትሕአለው፣ ርኆቦት ሰላሎ፣ ሙሴ ከበላ፣ ሳሙኤል ተስፋየ የመጀመርያ ልምምዳቸውን ሰርተዋል።
ቡድኑ አሁንም የቪዲዮ ተንታኝም ሆነ የአካል ብቃት አሰልጣኝ እንዳልያዘ የተመለከትን ሲሆን የቡድኑን ቀጣይ ልምምዶችን እየተመለከትን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

