የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ ልምምዱን እያከናወነ ባለበት ወቅት የመስመር አጥቂው ጉዳት አጋጥሞታል።
ከማላዊ አቻው ጋር ግንቦት 29 እና ሰኔ 2 በድሬዳዋ ስታዲየም የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በንግድ ባንክ ሜዳ የመጀመርያ ልምምዱን እያደረገ ባለበት ወቅት የመስመር አጥቂው ጉዳት አጋጥሞታል
ጉዳት ያስተናገደው ተጫዋች አዲስ ግደይ ሲሆን የብሔራዊ ቡድኑ የህክምና ባለሙያው ብሩክ ህክምና ቢያደርግለትም ሊሻለው ባለመቻሉ ልምምዱን አቋርጦ ወጥቷል። አዲስ ጉዳቱ ከብሔራዊ ቡድን ስብስብ ያስወጣው ይሆን የሚለው በህክምና ቡድኑ ውሳኔ የሚያስፈልገው ይሆናል።

እንደ ሶከር ኢትዮጵያ ዕይታ ከሆነ የአዲስ ግደይ ህመም ጡንቻው ላይ በመሆኑ እና በቂ እረፍት የሚያስፈልገው በመሆን ከብሔራዊ ቡድን ውጭ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።
አስቀድሞ መስፍን ታፈሰ በጉዳት ከቡድኑ ውጭ መሆኑ እና ዛሬ አዲስ ግደይ መጎዳቱን ተከትሎ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሰሀሌ በቀጣይ ለአዲስ ተጫዋች ጥሪ ያቀርባሉ ወይስ በዚህ ስብስብ ይቀጥላሉ የሚለው የሚጠበቅ ይሆናል።

