የመስመር አጥቂው ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጭ ሆኗል

የመስመር አጥቂው ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጭ ሆኗል

አስቀድመን ባደረስናቹሁ መረጃ መሰረት የመስመር አጥቂው ከብሔራዊ ቡድን ውጭ መሆኑ ታውቋል።

ከማላዊ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች ያሉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጀመርያ ልምምዱን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ከስምንት ሰዓት ጀምሮ መስራቱን ይታወሳል።

በልምምዱ ወቅት የመስመር አጥቂው አዲስ ግደይ ጡንቻው ላይ ጉዳት በማስተናገዱ ልምምዱን አቋርጦ መውጣቱን ገልፀንላቹሁ ነበር። አሁን ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ መሠረት የአዲስ ጉዳት ለቀጣዮቹ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደማያደርሰው እና ከሆቴል እንደወጣ አውቀናል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ከጠሯቸው 23 ተጫዋቾች መካከል ሁለቱ የመስመር አጥቂዎች መስፍን ታፈሰ እና አዲስ ግደይ በጉዳት ከቡድኑ ውጭ መሆናቸውን ተከትሎ አዲስ ተጫዋቾች ይጠራሉ ወይስ ባለው ስብስብ ይቀጥላሉ የሚለውን እንደከዚህ ቀደሙ ተከታትለን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።