የአምስት ዓመት የወላይታ ድቻ ቆይታ በኋላ ከክለቡ የተለያየው ግብጠባቂው ቢንያም ገነቱ መዳረሻው ፈረሰኞቹ ጋር ሆኗል
በወላይታ ድቻ ታዳጊ ቡድን መነሻውን ያደረገው ግብ ጠባቂው ቢንያም ገነቱ ያለፉትን አምስት ዓመታት በወላይታ ድቻ ያደረገውን ቆይታ ማጠናቀቁን ተከትሎ አሁን በግብጠባቂ ህይወቱ ሁለተኛ የሆነው ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመቀላቀቀል ተስማምቷል። ቢንያም የህክምና ምርመራውን ያጠናቀቀ ሲሆን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለሁለት አመት ለመጫወት ተስማምቷል።

