የዋልያዎቹ እና የቴራንጋ አናብስት ጨዋታ ማን ይመራል ?

የዋልያዎቹ እና የቴራንጋ አናብስት ጨዋታ ማን ይመራል ?

ካሜሩናዊው ዳኛ ዳግም የኢትዮጵያን ጨዋታ ይመራል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ወደ ደቡብ ሱዳን አቅንቶ ከሱዳን አቻው ጋር ለመጫወት በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መስከረም 19 ከሴኔጋል ጋር የማጣሪያ ውድድሩ ሁለተኛ ጨዋታ እንደሚያከናውን ይታወቃል። ይህ በባህርዳር ከተማ የሚደረገው ጨዋታ የሚመሩ ዳኞችም ታውቀዋል። በዚህ መሰረት በቅርቡ በተከናወነው የአፍሪካ ከ 17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ከ ሞሮኮ ጋር ያደረጉት ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመሩት ካሜሩናዊው ዋና ዳኛ ዊሊ ስቴፋን ንጋህ በዋና ዳኝነት እንዱሁም ቪንሰንት ንጊማዶህ እና ቦዞይ ኦሪያ በረዳት ዳኝነት ሲመደቡ አንድሬ ኦነሲሜ አራተኛ ዳኛ ሆነው ተመድበዋል።