አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የሊጉ የመጀመርያ ተሰናባች አሰልጣኝ ሆነዋል።

የ2019 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማሬው ያላማረለት ሀዲያ ሆሳዕና ገና በሊጉ ጅማሬ አምስት ጨዋታ ላይ አሰልጣኙን ያሰናበተ የመጀመርያ ክለብ መሆን ችሏል።
የክለቡ ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ቡድኑ እያስመዘገበው ባለው ውጤትም ሆነ እንቅስቃሴ ደስተኛ ባለመሆኑ ከውሳኔ አንደደረሰ የሰማን ሲሆን በጊዜያዊነት በምክትል አሰልጣኙ ታደሰ ጥላሁን እንዲቀጥል ተወስኗል።
ሀዲያ ሆሳዕና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በአራት ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለፍፃሜ ጨዋታ መድረሱ ይታወቃል።

