ዛምቢያ ለምታስተናግደው የ2017 የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ጋና ኢትዮጵያን 5-2 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ ወደ ተከታዩ የማጣርያ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡ ትላንት ሊደረግ የነበረው ጨዋታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ወደ ዛሬ በተላለፈው ጨዋታ ጋና 4-0 በማሸነፍ በመጀመርያው ጨዋታ የደረሰባትን የ2-1ሽንፈት ቀልብሳለች፡፡
የጋናን የድል ግቦች ያው ዮቦሃ (6 ፣ 75) ፣ ዳውዳ መሃመድ (9) እና ኢቫንስ ሜንሳህ (58) ከመረብ ያሳረፉ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የእለቱ ዳኛ ጨዋታውን የመራበት መንገድ ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
የቡድን መሪው ቾል ቤልም 4ኛው ግብ ከተቆጠረ በኋላ ከዳኛው ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡ ሲሆን በፀጥታ ሃይሎች ከመቀመጫቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፣ የቡድን መሪው እና ተጫዋቸችም ከጨዋታው በኋላ ለኤፍ ኤም አዲስ በሰጡት አስተያየት ዳውዳ መሃመድ እንየው ካሳሁንን በቡጢ ተማቶ በዝምታ መታለፉን እና ሌሎች የዳኝነት ችግሮችን በመጥቀስ የደረሰባቸውን ተጽእኖ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በነገው እለት ወደ አዲስ አበባ ጉዞውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሁለት ግብ ያስቆጠረው ያው የቦሃ