የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲጀምር ቦዲቲ ላይ ወላይታ ድቻ ከ መከላከያ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል፡፡ ቴዎድሮስ በቀለም ወንድወሰን አሸናፊ እና ወላይታ ድቻ ላይ በሁለተኛው ዙር ለመጀመርያ ጊዜ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል፡፡
በድንቅ የደጋፊዎች ድባብ እና ፈጣን እንቅስቃሴ በታጀበው ጨዋታ የግብ ቅድሚያውን የወሰዱት ወላይታ ድቻዎች ነበሩ፡፡ በ18ኛው ደቂቃ በድሉ መርዕድ ከቅታት ምት ያሻማውን ኳስ ቴዎድሮስ በቀለ በእጁ በመንካቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት አምበሉ አላዛር ፋሲካ ወደ ግብነት ቀይሯታል፡፡
መከላከያዎች ከግቡ መቆጠር በኋላ የአቻነት ግብ ለማግኘት ጫና ፈጥረው የተንቀሳቀሱ ሲሆን በ38ኛው ደቂቃ ለድቻ ግብ መቆጠር አስተዋፅኦ ያደረገው ቴዎድሮስ በቀለ ከማዕዘን የተሸገረውን ኳስ በግንባሩ በመግጨትመከላከያን አቻ አድርጓል፡፡ ይህች ግብ በሁለተኛው ዙር በወላይታ ድቻ ላይ የተቆጠረች የመጀመርያ ግብ ሆና ተመዝግባለች፡፡
የድቻው ግብ ጠባቂ ወንድወሰን አሸናፊ ከ930 ደቂቃዎች በላይ መረቡን ባለማስደፈር በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በርካታ ደቂቃ ግብ ያልተቆጠረበት ኢትዮጵያዊ ግብ ጠባቂ ለመሆን ችሏል፡፡ (የሊጉ ሪኮርድ የተያዘው በቅዱስ ጊዮርጊሱ ዩጋንዳዊ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ ነው፡፡)
የድቻ ደጋፊዎች ቡድናቸውን በዚህ መልኩ ሲያበረታቱ ነበር
የደረጃ ሰንጠረዥ
ቀሪ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፕሮግራም
ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2008
09፡00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ አዳማ ከተማ (ሀዋሳ)
11፡30 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አአ ስታድየም)
ረቡዕ ሰኔ 8 ቀን 2008
09፡00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ኤሌክትሪክ (ድሬዳዋ)
09፡00 ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ቡና (ይርጋለም)
09፡00 ዳሽን ቢራ ከ አርባምንጭ ከተማ (አዳማ አበበ ቢቂላ)
09፡00 ሀዋሳ ከተማ ከ ደደቢት (ሀዋሳ)