ይፋ ያልሆነ ፡ ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ጨዋታዎች በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ሲወሰንበት ለሀዋሳ ከተማ ፎርፌ ተሰጥቷል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባለፈው አርብ በአዲስ አበባ ስታድየም ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ የተከሰተው የስታድየም ረብሻን ተከትሎ በኢትዮጵያ ቡና ላይ ቅጣት ጥሏል፡፡

በቅታት ውሳኔው መሰረት ኢትዮጵያ ቡና ከ ሃዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ለሀዋሳ ፎርፌ (3 ነጥብ እና 3 ንፁህ ግብ) እንዲሰጥ ከውሳኔ የደረሰ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ የሚያካሂዳቸው 2 ጨዋታዎችን ማለትም ከወላይታ ድቻ እና ከድሬዳዋ ከተማ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎችን በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ከውሳኔ ተደርሷል፡፡ በረብሻው የወደሙ ንብረቶች ተተምነው ከፍያ እንዲፈፀምም ከውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቅጣት ውሳኔውን ይፋ ሲያደርግ ሙሉ ዘገባ ይዘን የምንመለስ ይሆናል፡፡

PicsArt_1465595306923

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *