ደደቢት የቻምፒዮንስ ሊግ ተጋጣሚውን አወቀ

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን ድልድል ይፋ ሲሆን ደደቢት ተጋጣሚውን አውቋል።

የአምናው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን በቅድመ ማጣርያው ከዛንዚባሩ ሻምፒዮን ኬ ኤም ኤም ኬ ጋር ተደልድሏል፡፡ የመጀመርያው ጨዋታን ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው ደደቢት የመልሱን በሜዳው የሚያከናውን መሆኑ ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ ምቹ አጋጣሚ ይፈጥረለታል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ድልድል በፅፅር ቀለል ያለ ቢመስልም የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ይህንን ዙር ካለፈ የቱኒዚያውን የ2013 ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊ ስፖርቲ ሴፋክሲያን ማግኘቱ ነው፡፡ የቱኒዚያው ክለብ ባለፈው የውድድር ዘመን ቅ/ጊዮርጊስን በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ አዲስ አበባ ላይ በደጋፊው ፊት 3-1 ማሽነፉ ይታወሳል፡፡

©Soccer Ethiopia