በሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ውድድር በሴቶች ደቡብ ፣ በወንዶች ቤኒሻንጉል አሸናፊ ሆነዋል

አራተኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና የምዘና ውድድር ከነሃሴ 18-29 በሃዋሳ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በ13 የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ በቆየው በዚህ ውድድር በእግርኳስ በሴቶች 7 ፣ በወንዶች ደግሞ 9 ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ተሳታፊ ሆነዋል። በወንዶች ቤኒሻንጉል ፣ በሴቶች ደቡብ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

PicsArt_1472992339439

ትላንት በተከናወነው የሴቶች የፍጻሜ ጨዋታ ደቡብ ክልል አማራ ክልልን 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፎ የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ በተከናወነ የደረጃ ጨዋታ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ 4-3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

PicsArt_1472992437541

የወንዶቹ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ሲቀጥል የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት ውድድሩ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል።

ሁለት ሰዓት ላይ ለደረጃ የተከናወነው የኦሮሚያ ክልል እና የድሬዳዋ ጨዋታ በኦሮሚያ 7-2 አሸናፊነት ተጠናቋል። ከደረጃው ጨዋታ በመቀጠል በተከናወነው የፍጻሜ ጨዋታ ደቡብ እና ቤንሻንጉልን ሲያገናኝ ጨዋታው በቤንሻልጉል 4-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ በኦሎምፒክ መርህ መሰረት አሸናፊ ለሆኑ ቡድኖች እንደየደረጃቸው የወርቅ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያዋች ተሸልመዋል፡፡
ከዚህ ውድድር ላይ ባሳዩት ድንቅ አቋም ለኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ቡድን ከአስር በላይ ተጨዋቾች የተጠሩ ሲሆን ከቡድኑ ጋር ተቀላቅለው የMRI ምርመራን ካለፉና ብሄራዊ ቡድኑ በሀዋሳ በሚያደርገው ዝግጅት አሰልጣኙን የሚያሳምኑ ከሆነ ሊመረጡ እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏዋል።

ከዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ ከነበሩ ቡድኖች ውስጥ ጋምቤላና ሃረሪ በእድሜ ተገቢ ያልሆኑ ተጨዋቾች በማሰለፍ ከውድድሩ በቀጥታ እንዲሰናበቱ ተደርጎዋል።

በመጨረሻም ከውድድሩ አላማና ግብ አንጻር በትክክል የወደፊት ተተኪ የእግር ኳስ ተጨዋቾችን ለማግኘት የእድሜ ጉዳይ ሊጤንበት እንደሚገባ መልክታችን ነው።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *