ታክቲካዊ ትንታኔ ፡ ኢትዮጵያ ቡና 2-0 መከላከያ

በ11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና መከላከያን አሸንፎ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ የሶከር ኢትዮጵያውሚልኪያስ አበራ ጨዋታውን ተመልክቶ የሚከተለውን ታክቲካዊ ትንታኔ አዘጋጅቷል፡፡

ባለፈው ሳምንት ከሜዳው ውጪ ነጥብ ጥሎ የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና በ11ኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር በአበበ ቢቂላ ስታድየም አከናውኖ ድል አድርጓል፡፡

በጨዋታው የኢትዮጵያ ቡና በቴክኒክ ክህሎት የበለፀጉ አማካዮችን ባቀፈው የመሃል ክፍል የታገዘ 4-1-4-1 የተጫዋቾች የሜዳ ላይ አደራደር ጨዋታውን ሲጀመር በአበበ ቢቂላ ተከታታይ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መከላከያ ደግሞ ጠባቡን 4-4-2 ተጠቅሟል፡፡

(ምስል 1)

buna mek 1

የመጀመርያው አጋማሽ

በግዜ ሒደት ከፍተኛ መሻሻልን እያሳዩ የመጡት የቡና የመስመር ተtከላካዮች (አህመድ ረሺድ እና ሮቤል ግርማ) በጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና የማጥቃት እንቅስቃሴ (Attacking Phase) የነበራቸው ሚና የጎላ ነበር፡፡ በጥሩ የቦታ አያያዝ (Positioning) ፣ የቡድናቸውን የማጥቃት አጨዋወት የሚያግዘው የፊት ለፊት ጊዜውን የጠበቀ እንቅስቃሴ (overlapping movement) እና ቡድኑ በመስመር ላይ ለሚኖረው የተጫዋቾች የቁጥር ብልጫ (Overloading) ያሳዩት ትጋት ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡

በእርግጥ የተጋጣሚያቸው መከላከያ የመስመር አማካዮች (ሳሙኤል ታዬ እና ፍሬው ሰለሞን ) በተደጋጋሚ በመሃለኛው የሜዳ ክፍል መገኘታቸውና በቡና የግበ ክልል (ሳጥኑ አካባቢ) ያተኮረ እንቅስቃሴ የነበራቸው አጥቂዎቹ (ምንይሉ ወንድሙ እና መሃመድ ናስር) ለሮቤልና አህመድ የበለጠ ነፃነትን ሰጥቷቸዋል፡፡

አጥቂዎች በሜዳው የጎንዮሽ እንቅስቃሴ ለቡድናቸው በላይኛው የሜዳ ክፍል የ WIDTH ን ጥቅም የማስገኘት ሐላፊነት እንዲሁም የተጋጣሚን ፉልባኮች አፍኖ የመያዝ (stifle የማድረግ) እድሉ ቢኖራቸውም የመከላከያ አጥቂዎች ይህንን ሲያደርጉ አልተስተዋለም፡፡ የአሰልጣኝ ገብረመድን ቡድን የመስመር ተከላካዮች (ዮሃንስ እና ሽመልስ) በቡድናቸው የማጥቃት እንቅስቀሴ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ቢኖራቸውም በመስመር አማካዮቻቸው ሲታገዙ አይታይም፡፡ በሜዳው ቁመት ሰፊ ርቀትን እንዲሸፍኑ በመደረጋቸው በቶሎ ትተውት የሚሄዱትን ክፍተት ለመሸፈን ተቸግረዋል፡፡በተለይ ሳሙኤል በአብዛኛው በመሃል ሜዳ በማሳለፉ ሽመልስ OVERLAP በሚያደርግበት ወቅት በመስመሩ ብቻውን ሲሆን ይታያል፡፡በግራ መስመር ዮሃንስ እና ፍሬው በመከላከል ቅርፅ (Defending Shape) ተቀራርበውበመጫወት የተጋጣሚን የመቀባበያ አማራጭ በማጥበብ የተሸለ ተንቀሳቅሰዋል፡፡

የመሃል ተከላካዮቹ ተሰስፋዬ እና ሲሳይ የበለጠ ወደ ሽመልስ (ወደ ቀኝ መስመር) አድልተው በመጫወታቸው በግራው በኩል በመስመር ተከላካይ እና በመሃል ተከላካይ መሃል (Through the channels) ያለው ክፍተት እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ ይህም አስቻለው ግርማን የበለጠ ራሱን ነፃ አድርጎ ኳስን የሚቀበልበትን መንገድ አመቻችቶለታል፡፡ ባገኘው ክፍተትም የቡናን የቀኝ መስመር የማጥቃት ሽግግር (Attacking flank transition) በፍጥነት እንዲያስጀምር ሲያግዘው ታይቷል፡፡ ከተከላካዮች ጀርባ ያለውን ክፍተትና HALF SPACE የመጠቀም አቅሙ ቡና በማጥቃት እንቅስቃሴ ለነበረው የበላይነት አይነተኛ ሚና ነበረው፡፡

በጨዋታው ቡናዎች የግብ ሙከራዎችን የሚያደርጉበት መንገድ ማራኪ ነበር፡፡ በአማካዮቹ የቴክኒክ ችሎታ ላይ የተመረኮዙት አጭር ቅብብሎች ወደ መከላከያ ይግብ ክልል የሚደርሱትበት መንገድ የሚስብ አይነት ነው፡፡ በ11ኛው ደቂቃ ያደረጓት የግብ ሙከራ ሒደት ለዚህ እንደማሳያ ሊቀርብ ይችላል፡፡ የሮቤል ፣ መስኡድ ፣ ዳዊት ፣ ኤለልያስ ፣ ቢንያም እና አስቻለው አስደሳች ቅብብል የተደረገበት የግብ ሙከራ በጀማል ጣሰው ቢከሽፍም መራኪ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ቡና የመሃል ተከላካዮች ኤፍሬም እና ኦሊቨር ዋረን የመናበብ እና ተደጋጋሚ የመደነጋገር ችግር ተስተውሎባቸዋል፡፡ መከላከያዎች ከ20 – 40ባለው ደቂቃ ውስጥ ለሞከሯቸው ኳሶችም የተከላካዮቹ ድክመት አስተዋፅኦው የጎላ ነው፡፡ በእለቱ መልካም አቋም ያሳየው ጌቱ ተስፋዬ የመሃመድን (21ኛው ደቂቃ) ፣ የሽመልስን (36ኛው ደቂቃ) እና የምንይሉን (38ኛው ደቂቃ) የመለሰበት መንገድ ጥሩ የሚባል ነው፡፡

ኢትዮጵያ ቡናዎች የመጀመርያ ግባቸውን ያገኙት አስቻለው ከተከላካዮች ጀርባ በሚገኘው ክፍተት ላይ በነበረው ተፅእኖ ነበር፡፡ በተፈፀመበት ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምትም አጥቂው ቢንያም አሰፋ በጥሩ ሁኔታ ከመረብ አሳርፎ የመጀርያውe አጋማሽ በኢትዮጵያ ቡና 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

ምስል 2

buna mek 2

ሁለተኛው አጋማሽ

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በዚህኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሙሉአለም ጥላሁንን ቀይረው በማስገባት የሮቤል ግርማን እንቅስቃሴ ለመግታት ከመሞከራቸውም በላይ አጥቂው በማጥቃት ወረዳው (attacking Third) ለቡድኑ የሚያበረክተውን ሰፊ የማጥቃት ማእዘናት (Attacking angles) ለመጠቀም ሞክረዋል፡፡ሙሉአለም ከገባ በኋላ ሳሙኤል በይበልጥ ወደ ፊት እና ወደመስመር በመጠጋት ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሏል፡፡ መከላከያ ተክለወልድን የበለጠ ወደ ኋላ በመሳብ እና ፉልባኮችን ይበልጥ እንዲያጠቁ በመፍቀድ ይበልጥ በማጥቃተ ላይ ያተኮረ ለ4-1-3-2 የቀረበ መልክን ይዞ ቀርቧል፡፡

ኢትዮጰያ ቡናዎች ደግሞ ደረጄን ባፈገፈገ የተከላካይ አማካይነት ሚና የበለጠ የመከላከል ሐላፊነት በመስጠትና አማካዮች በሜዳው ቁመትማ ሆነ በጎንዮሽ የሚኖራቸውን ክፈተት በማጥበብ (horizontal compactness and vertical compactness) የጥንቃቄ ጨዋታን ሲያከናውኑ ነበር፡፡ ከእረፍት በፊት ቡናዎች በተደጋጋሚ የተጫዋቾች ቅይይር (የቦታ) እና ወደ አንድ መስመር በዛ ብለው በመታየት ሌላውን መስመር ተጋላጭ ሲያደርጉ ነበር፡፡ነገር ግን በሁለተኛው አጋማሽ በአንድ መስመር መደራረብን አስቀርተውና በታክቲክ ዲሲፕሊን (በመከላከል እና በማጥቃት) ተሸለው ታይተዋል፡፡ ቢንያም አሰፋ ወደ ኋላ እየተመለሰ የቡድኑን የአማካይ ተጫዋቾች በመከላከል አጨዋወት ሲረዳና በግራ መስመረ አድልቶ የመቀባበያ አማራጮችን (Passing lane options) ሲያሰፋ ነበር፡፡

(ምሰል 3)

buna mek 3

የቡና SQUEEZING PLAY

በናዎች ከእረፍት መልስ ያደረጋቸው የተጫዋች ቅያሪዎች የበለጠ የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት እንቅስቀሴ ላይ እንዲያተኩሩ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ ተከላካዮቹ ወደ መሃል ቀርበው እየተጫወቱ አማካዮቹ እና አጥቂው ወደኋላ ተመልሰው ሲንቀሳቀሱ በመስመሮች መካከል የሚፈጠረውን ክፍተት ሲያጠቡ ነበር፡፡ ይህም የመከላከያ አጥቂዎችን Depth (የተጋጣሚ ተከላካዮችን ወደራሳቸው ክልል እንዲመለሱ ማስቻል) ያሳጣ ነበር፡፡ በአብዛኛው ሁለቱ መስመሮች (ተከላካዩ እና አማካዩ) ከኳስ ጀርባ በመሆን ጥሩ ሲከላከሉ ውለዋል፡፡ ቡድኑ በመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴው ወይም ከመከላከል ወደ ማጥቃት ባደረገው ሽግግር ላይe በላይኛው ሜዳ ብዙ ተጫዋቾችን ያለማግኘቱ ምክንያት እና የሽግግሩ ፍጥነት ማነስም ከዚህ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡ COMPACT DEFENDING ለማከናወን የሚያሳትፏቸው ተጫዋቾች መብዛታቸው በመለሶ ማጥቃት ላይ የሚኖራቸውን ተሳትፎም ቀንሶታል፡፡ሆኖም በ93ኛው ደቂቃ የመከላከያ ተጫዋቾች ለማጥቃት ከግብ ክልላቸው ነቅለው ሲወጡ ያገኙትን ክፍተት ተጠቅመውበታል፡፡ አህመድ ረሺድ በግራ መስመር ከራሳቸው የግብ ክልል የተላከችን ኳስ ባገኘው ሰፊ ክፍተት ተጠቅሞ ይድነቃቸው (በጀማል ተቀይሮ የገባ ግብ ጠባቂ) አልፎ ያስቆጠራት የማሳረግያ ግብ ውብ ነበረች፡፡ የቡናዎችእስከመጨረሻው ደቂቃ የመታገልና የአሸናፊነት ስሜትም ለቡድኑ የ2-0 ድል አይነተኛ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡

ምሰል 4


buna mek 4

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *