የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ዙር በመጪው መጋቢት 5 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ በመጋቢት ወር በሚካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ቻምፒዮና ምክንያት ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሊጉ የአዲስ አበባ ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታድየም የሚደረጉ ይሆናል፡፡
የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎቹ እስከ ነሃሴ 7 ድረስ የሚደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎችን የሚጀምረው በሰኔ ወር በመሆኑ ፌዴሬሽኑ የሊጉ ጨዋታዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እንዳቀደ ተነግሯል፡፡
የ2ኛው ዙር ጨዋታዎች የሚካሄዱባቸው ሳምንታት የሚከተሉት ናቸው፡-
14ኛ ሳምንት – መጋቢት 5 እና 6
15ኛ ሳምንት – መጋቢት 12 እና 13
16ኛ ሳምንት – መጋቢት 19 እና 20
17ኛ ሳምንት – መጋቢት 26 እና 27
18ኛ ሳምንት – ሚያዝያ 3 እና 4
19ኛ ሳምንት – ሚያዝያ 10 እና 11
20ኛ ሳምንት – ሚያዝያ 17 እና 18
21ኛ ሳምንት – ሚያዝያ 25 እና 26
22ኛ ሳምንት – ግንቦት 1 እና 2
23ኛ ሳምንት – ግንቦት 8 እና 9
24ኛ ሳምንት – ግንቦት 22 እና 23
25ኛ ሳምንት – ግንቦት 29 እና 30
26ኛ ሳምንት – ሰኔ 6 እና 7