ከ10 አመታት የየመን ቆይታ በኋላ ወደ ሃገር ቤት ተመልሶ የቀድሞ ክለቡ ኤሌክትሪክን የተቀላቀለው ዮርዳኖስ አባይ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ፕላኔት ስፖርት የሬድዮ ፕሮግራም ዘግቧል፡፡
ለዮርዳኖስ እና ክለቡ መለያየት እንደ ምክንያት የተቀመጠው ከክለቡ አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ጋር የፈጠረው አለመግባባት መሆኑ ታውቋል፡፡ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 1-0 በረታበት የሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ ላይ አለመሰለፉም ላለመግባባታቸው ምክንያት መሆኑ ተነግሯል፡፡
የ3 ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ አገቢው ዮርዳኖስ አባይ ኤሌክትሪክን የተቀላቀለው በአጭር ኮንትራት ሲሆን ዘንድሮ ሁለት የሊግ ግቦችን አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አቀብሏል፡፡