በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵጵን የሚወክለው ቅዱስ ጊየርጊስ የመልስ ጨዋታቸውን በባህርዳር ብሄራዊ ስታድየም ማከናወን እንደሚችሉ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለኢንተርናሽናል ውድድሮች ያስመዘገበው ሜዳ አዲስ አበባ ስታድየም ቢሆንም የመዲናዋ ስታድየም ለአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ቻምፒዮና ውድድር በእድሳት ላይ የሚደረግ በመሆኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአልጄርያው ኤም ሲ ኡልማ ጋር ፌብሩወሪ 29 የሚያደርገው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታን ማስተናገድ አይችልም፡፡
የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽንስ ዋንጫ የመጀመርያ ጨዋታ ከፌብሩወሪ 13 እስከ 15 የሚካሄድ ሲሆን የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከፌብሩወሪ 27 እስከ ማርች 1 ባሉት ቀናት ውስጥ ይካሄዳል፡፡
ምንጭ – ፕላኔት ስፖርት