ኮንፌድሬሽን ካፕ: ደደቢት ከሜዳው ውጪ ድል ቀናው

በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ካፕ እየተወዳደረ የሚገኘው የኢትዮጵያው ተወካይ ደደቢት የሲሸልሱን ኮት ዲ ኦርን በስታደ ደ አሚቴ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የፓርስሊን ክለብ የሆነው ኮት ዲ ኦር በ34ኛው ደቂቃ በዳርዊን ሮዜት ግብ መሪ መሆን ችሎ ነበር፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ የደደቢቱ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ናይጄሪያዊውን ሳሙኤል ሳኑሚ በበረከት ይሳቅ ቀይረው በማስገባት የተሻለ ውጤት ይዘው ወጥተዋል፡፡ ለደደቢት የማሸነፊያ ግቦችን ዳዊት ፍቃዱ እና ሳሙኤል ሳኑሚ በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡ዳዊት ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል እንዲሁም አንድ ለጎል የሚሁን ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ኮኮብ ሆኖ ወጥቷል፡፡

ኮት ዲ ኦር የጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ ባስቆጠሩት ሁለተኛ ግብ ጨዋታው 3ለ2 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ደደቢት ኮት ዲ ኦርን አሸንፎ ወደ ቀጣይ ዙር ካለፈ ከናይጄሪያው ዋሪ ዎልቭስ ወይም ከቡርኪና ፋሶው አርሲ ቦቦ ዲኦላሶ ጋር የሚጋጠም ይሆናል፡፡ ዋሪ ዎልቭስ በመጀመሪው ጨዋታ ከሜዳው ውጪ አርሲ ቦቦ ዲኦላሶን አቡ አዚዝ ጎል አሸንፏል፡፡ ደቢቢት የመልሱን ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኃላ በባህር ዳር ስታዲየም ያደርጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *