አሁን አሁን በርካታ ኢትዮጵያውያን በመላው አለም እግርኳስን ሲጫወቱ መመልከት አዲስ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም በየመን እና ቤተ እስራኤላውያን ደግሞ በእስራኤል ሲጫወቱ የተመለከትን ሲሆን በቀጣይ ጥቂት አመታት ውስጥ ደግሞ የደቡብ አውሮፓዊቷ ሃገር ጣልያን ኢትዮጵያውያን በብዛት የሚታዩበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በሁለቱ የሚላን ክለቦች አካዳሚ ውስጥ ብቻ 17 ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ
በኤሲ ሚላን በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ማለትም ከ19አመት በታች እስከ 10 አመት በታች በሚገኙ አካዳሚዎች ውስጥ በኢትዮጵያ የተወለዱ 12 ተጫዋቾች ይገኛሉ፡፡ በማደጎነት የተወሰዱና በጣልያናዊ ቤተሰባቸው የቤተሰብ ስም የሚጠሩ ናቸው፡፡
ለዛሬ በኤሲ ሚላን አካዳሚ ውስጥ በትንሹ የእድሜ እርከን ስር በሚገኙት ኢሶርዲንቴ 2003 (በ2003 የወለዱ ተጫዋቾችን ያቀፈ) እና ኢሶርዲንቴ 2004 (በ2004 የተወለዱ ተጫዋቾችን ያቀፈ) የሚገኙ 5 ተጫዋቾችን እናስተዋውቃችሁ፡፡
ኢሶርዲንቴ 2004
ስም – አበበ ሉስቼቲ
የትውልድ ስፍራ – አሶሳ (ቤኒሻንጉል ጉምዝ)
የትውልድ ዘመን – ኦክቶበር 17 ቀን 2004
እድሜ – 10
የሚጫወትበት ቦታ – አማካይ
ስም – አሰግድ ኢቫን
የትውልድ ቦታ – ሀዋሳ (ደቡብ)
የትውልድ ቀን – ሴፕቴምበር 25 ቀን 2004
እድሜ – 10
የሚጫወትበት ቦታ – አጥቂ
ኢሶርዲንቴ 2003
ስም – አማኑኤል አስፔሳኒ
የትውልድ ቦታ – ወላይታ (ደቡብ)
የትውልድ ቀን – ኖቬምበር 12 2003
እድሜ – 11
የሚጫወትበት ቦታ – አጥቂ
ስም – በኃይሉ ቱቺ
የትውልድ ቦታ – ካምባታ (ደቡብ)
የትውልድ ቀን – ዲሴምበር 30 ቀን 2003
እድሜ – 11
የሚጫወትበት ቦታ – ተከላካይ
ስም – አማኑኤል ፒሴሎ
የትውልድ ቦታ – አዲስ አበባ
የትውልድ ቀን – ሜይ 1 ቀን 2003
እድሜ – 11
የሚጫወትበት ቦታ – ተከላካይ