FTኤሌክትሪክ0-0አዳማ ከተማ
በተመሳሳይ ሰአት የተደረጉ ጨዋታዎች
FT’ ሀዋሳ ከተማ 3-3 ወላይታ ድቻ
FT’ ጅማ አባ ቡና 2-0 ሲዳማ ቡና
FT’ አርባምንጭ ከተማ 1-1 ደደቢት
ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ተሳተ!!!
90+4′ ሙጂብ ቃሲም የፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ !!
ፍጹም ቅጣት ምት!
90+3′ በቡልቻ ሹራ ላይ በተሰራ ጥፋት አዳማ ከተማ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
ዳዋ ሁቴሳ ወጥቶ ቡልቻ ሹራ ገብቷል
ቢጫ ካርድ
77′ ሙሉአለም ጥላሁን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
74′ ፍጹም ገብረማርያም ወጥቶ አቤል አክሊሉ ገብቷል፡፡
73′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ጃኮ ሲተፋው ሙሉአለም አግኝቶ ቢያስቆጥርም ጃኮ፡ላይ ጥፋተት ተሰርቷል በሚል ሳየይጸድቅ ቀርቷል፡፡
66′ ከጃኮ ፔንዜ በረጅሙ የተለጋውን ኳስ ሙጂብ ቃሲም ተቆጣጥሮ ቢሞክርም ሱሌይማን አቡ መልሶበታል፡፡
60′ ጨዋታው አሰልቺ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ ስኬታማ ያልሆኑ ረጃጅም ኳሶች እና ሙከራ አልባ ጨዋታ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡
47′ ጨዋታው ጉሽሚያ ታክሎበት ቀጥሏል፡፡ የጨዋታው ዳኛም የሃይል አጨዋወቶቸችን በዝምታ እያለፉ ይገኛል፡፡
ተጀመረ!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በሙሉአለም ጥላሁን አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
የእረፍት ሰአት ለውጥ – አዳማ
አዲስ ህንጻ ወጥቶ ሚካኤል ጆርጅ ገብቷል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡
ቢጫ ካርድ!
45+2′ ጥላሁን ወልዴ በአሸናፊ ሽብሩ ላይ በገባው አደገኛ ሸርታቴ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ 2-2 በሆነ ውጤት እረፍት ወጥተዋል፡፡
45′ ሲሳይ ቶሊ ከቅጣት ምት ያሻገረውን ኳስ አዲስ ህንፃ በግምባሩ በመግጨት ሞክሮ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
43′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ሙጂብ ሞክሮ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
43′ በርካታ የአዳማ ከተማ ደጋፊዎች በሚስማር ተራ ተሰብስበው ቡድናቸውን እየያበረታቱ ይገኛሉ፡፡
42′ ጨዋታው በተደጋጋሚ የዳኛ ፊሽካ እየተቆራረጠ ይገኛል፡፡
37′ ጅማ ላይ ጅማ አባ ቡና በቢያድግልኝ ኤልያስ ግብ 1-0 እየመራ ይገኛል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
ታፈሰ ተስፋዬ ወጥቶ ጥላሁን ወልዴ ገብቷል፡፡
33′ አዲስ ነጋሽ ከሳጥኑ የግራ ጠርዝ የመታውን ኳስ ጃኮ በግሩም ቅልጥፍና ወደ ውጪ አውጥቶታል፡፡ ግሩም ሙከራ ! ግሩም ግብ ጠባቂ!
28′ አርባምንጭ ላይ ደደቢት በጌታነህ ከበደ ግብ አርባምንጭ ከተማን 1-0 እየመራ ይገኛል፡፡
ቢጫ ካርድ
28′ ተስፋዬ መላኩ በብሩክ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
25‘ ፍጹም ገብረማርያም የሞከረው ኳስ የግቡን ቋሚ ታኮ ወጥቷል፡፡
24′ ሀዋሳ ላይ ወላይታ ድቻ መላኩ ወልዴ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠረው ግብ 1-0 እየመራ ይገኛል፡፡
20′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ አዲስ ህንፃ በግምባሩ ገጭቶ በግቡ አናት ለጥቂት ወጥቷል፡፡
15′ የጨዋታው የመጀመርያ 15 ደቂቃ የተቀዛቀዘ እና ከመሀል ሜዳ ያልዘለለ እንቅስቃሴ ታይቶበታል፡፡
9′ ሙጂብ ቃሲም ከግቡ የቀኝ ጎን አክርሮ የመታውን ኳስ ሱሌይማን መልሶበታል፡፡ የመጀመርያ አስደንጋጭ ሙከራ!
ተጀመረ!!
ጨዋታው በኤሌክትሪክ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
የመጀመሪያ አሠላለፍ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
22. ሱሌይማን አቡ
11. አወት ገ/ሚካኤል- 5 . አዲስ ነጋሽ (አምበል) – 21. በረከት ተሰማ – 15. ተስፋዬ መላኩ
23. አሸናፊ ሽብሩ -10. ዳዊት እስጢፋኖስ – 24. ዋለልኝ ገብሬ
16. ፍፁም ገ/ማርያም – 18 . ሙሉአለም ጥላሁን – 4. ኢብራሂም ፎፋኖ
ተጠባባቂዎች
1 ኦኛ ኦሜኛ
19 ደረጄ ሀይሉ
9 ብሩክ አየለ
14 ስንታየሁ ሰለሞን
12 ትዕዛዙ መንግስቱ
2 አቤል አክሊሉ
8 በሃይሉ ተሻገር
የመጀመርያ አሰላለፍ – አዳማ ከተማ
1.ጃኮ ፔንዜ
23.እሸቱ መና – 5.ተስፋዬ በቀለ – 4.ምኞት አበበ – 13.ሲሳይ ቶሊ
14.ብሩክ ቃልቦሬ – 19 ፋሲካ አሰፋው – 21.አዲስ ህንጻ
17.ሙጂብ ቃሲም – 10.ታፈሰ ተስፋዬ (አምበል) – 12.ዳዋ ሁቴሳ
ተጠባባቂዎች
79 .ሲሳይ ባንጫ
20 ሞገስ ታደሰ
14 በረከት ደስታ
15.ጥላሁን ወልዴ
18 ቡልቻ ሹራ
7 ሱራፌል ዳኛቸው
9.ሚካኤል ጆርጅ