ሀዋሳ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTሀዋሳ ከተማ1-1ቅዱስ ጊዮርጊስ

15′ ጋዲሳ መብራቴ | 68′ ራምኬል ሎክ


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ቢወጣም የሊጉን መሪነት ከአዳማ ተረክቧል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ ከተማ
89′ ዳንኤል ደርቤ ወጥቶ ፍርድአወቅ ሲሳይ ገብቷል፡፡

89′ ጃኮ አረፋት ከጋዲሳ የተቀበለውን ኳስ ሞክሮ ፍሬው በቀላሉ ይዞበታል፡፡

88′ ጋዲሳ መብራቴ ሀዋሳን መሪ ሊያደርግ የሚችል መልካም አጋጣሚ አምክኗል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
87′ ጊዮርጊስን አቻ ያደረገው ራምኬል ሎክ ወጥቶ ደጉ ደበበ ገብቷል፡፡

85′ ፍሬው ሰለሞን ከመሀል ወደ ሳጥን እየገፋ ገብቶ የመታው ኳስ የግቧን ቋሚ ነክታ ወጣለች፡፡

81′ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዋሳ የተሻሉ የግብ አጋጣሚዎችን እየፈጠረ ነው፡፡

78′ ጋዲሳ መብራቴ ከቀኝ መስመር ያሻገረውን ኳስ ጃኮ አረፋት በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጣበት፡፡

ቢጫ ካርድ
73′ መሀሪ መና ጃኮ አረፋት ላይ ጥፋት በመፈፀሙ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

70′ ራምኬል ሎክ ከማዕዘን ያሻማውን ኳስ ምንተስኖት በግንባሩ ገጭቶ አግዳሚውን ነክታ ወጥታለች፡፡ጊዮርጊስ ጫና ፈጥሮ እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ጎልልል! ጊዮርጊስ
68′ አብዱልከሪም ኒኪማ ያሻገረውን ራምኬል ሎክ ቄንጠኛ በሆነ መልኩ መትቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡

67′ ደስታ ዮሀንስ በድንቅ ሁኔታ አልፎ ያቀበለውን ኳስ ጃኮ አረፋት በሚያስቆጭ ሁኔታ ስቶታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
64′ ኤፍሬም ዘካሪያስ ወጥቶ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኃላ ግርማ በቀለ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
62′ አቡበከር ሳኒ ወጥቶ ሳላሀዲን ሰይድ ገብቷል፡፡

57′ ታፈሰ ሰለምን ሳጥን ውስጥ ተጠልፎ ወድቆ ዳኛው ፍጹም ቅጣት ምት አልሰጡም በማለት ደጋፊዎች ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

53′ አዳነ ግርማ ከግብ ጠባቂው ሜንሳ ጋር ተገናኝቶ አገባው ሲባል በሚገርም ሁኔታ መሳይ ጳውሎስ ነጥቆታል፡፡ መሳይም ከደጋፊዎች አድናቆትን አግኝቷል፡፡
46′ አብበከር ሳኒ የመታውን ኳስ ሶሆሆ በድንቅ ሁኔታ አወጣበት፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጫወታ ክፍለ ጊዜ በሀዋሳ ከተማ አማካይነት ተጀመረ፡፡


እረፍት !
የመጀመርያው አጋማሽ በሀዋሳ የበላይነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

45′ ፍሬው ሰለሞን በአስደናቂ ሁኔታ በቀጥታ የመታውን ኳስ ፍሬው አውጥቶበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
44′ ፍሬዘር ካሣ ወጥቶ አንዳርጋቸው ይላቅ ገብቷል፡፡

43′ ደስታ ዮሀንስ ከጋዲሳ ጋር በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ግብ ገብተው ያቀበሉትን ታፈሰ ሰለሞን መትቶ በግቡ ቋሚ ታካ ወጣለች፡፡

42′ መሀሪ መና ያሻገረውን ኳስ አብድልከሪም ኒኪማ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

40′ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ተደጋጋሚ ጥፋት እየፈጸሙ በዝምታ ታልፈዋል በሚል የሀዋሳ ደጋፊ ዳኛውን እየተቃወሙ ይገኛል፡፡

ቢጫ ካርድ
34′ ፍሬዘር ካሣ ጋዲሳ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

29′ ፍሬው ሰለሞን ዳግም በድንቅ ሁኔታ ያቀበለውን ኳስ በድጋሚ ጃኮ መትቶ ግብ ጠባቂው ፍሬው አውጥተቶበታል፡፡

27′ ፍሬው ሰለሞን በግሩም ሁኔታ ያቀበለውን ግልፅ የግብ እድልን ጃኮ አራፋት ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

ጎልልል!!! ሀዋሳ
15′ ጋዲሳ መብራቴ ከደስታ ዮሀንስ የተላከለትን ኳስ በግል ጥረቱ እየገፋ ገብቶ በማስቆጠር ሀዋሳን መሪ አድርጓል፡፡

7′ ራምኬል ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ አብድልከሪም ንኪማ መትቶ ሜንሳህ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

5′ ሀዋሳ ከተማ ጫና ፈጥሮ እየተጫወተ ይገኛል፡፡

2′ ደስታ ዮሀንስ በግል ጥረቱ ያሻገረውን ኳስ አራፋት ጃኮ በግንባሩ በመግጨት ሞክሮ ለጥቂት ወጣለች፡፡

ተጀመረ!!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አማካይነት ተጀምሯል፡፡


9:00 ቅዱስ ጊዮርጊሶች በአዳነ ግርማ አማካኝነት ለክብረአብ ዳዊት ቤተሰቦች የገንዘብ ስጦታ አበርክተዋል፡፡

8:50 ይህን ጫወታ በዋና ዳኝነት ፌድራል ዳኛ ተካልኝ ለማ ፤ ረዳቶቻቸው ፌድራል ዳኞች ካሣሁን ፍፁም እና አንድነት ዳኛቸው እንዲሁም 4ኛ ዳኛ ፀጋዬ ቶርባ ፤ ኮሚሽነር ጌታቸው የማነ ብርሀን ይሆናሉ፡፡

8:34 የሁለቱም ክለብ ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው ሲያሟሙቁ በደጋፊዎቻቸው ህብረ ዜማ ደምቋል፡፡



የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ

1 ሶሆሆ ሜንሳ

7 ዳንኤል ደርቤ – 13 መሳይ ጳውሎስ – 22 መላኩ ወልዴ – 12 ደስታ ዮሀንስ

24 ኃይማኖት ወርቁ – 3 ኤፍሬም ዘካርያስ

5 ታፈሰ ሰለሞን – 10 ፍሬው ሰለሞን – 11 ጋዲሳ መብራቴ

15 ጃኮ አራፋት


ተጠባባቂዎች

30 አላዛር መርኔ
4 አስጨናቂ ሉቃስ
8 ግርማ በቀለ
14 ወንድሜነህ አይናለም
17 መድሀኔ ታደሰ
26 ወንድማገኝ ማዕረግ
27 ፍርዳወቅ ሲሳይ



​የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

1 ፍሬው ጌታሁን

2 ፍሬዘር ካሳ – 15 አስቻለው ታመነ – 13 ሳላሀዲን ባርጊቾ – 3 መሀሪ መና

23 ምንተስኖት አዳነ – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 27 አብዱልከሪም ኒኪማ

10 ራምኬል ሎክ – 19 አዳነ ግርማ – 18 አቡበከር ሳኒ


ተጠባባቂዎች

22 ዘሪሁን ታደለ
4 አበባው ቡታቆ
7 ሳላዲን ሰኢድ
12 ደጉ ደበበ
20 ዘካርያስ ቱጂ
24 ያስር ሙገርዋ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *