በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ካፕ አንደኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ደደቢት ነገ ዋሪ ዎልቭስን በባህርዳር ስታድየም ያስተናግዳል፡፡
በመጀመርያው ጨዋታ 2-0 ተሸንፎ የተመለሰው ደደቢት ውጤቱን ቀልብሶ ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ ፈተና ይገጠመዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በጨዋታው በደደቢት በኩል ጋናዊው ግብ ጠባቂ ሱሌማና አቡበከር እና ያሬድ ዝናቡ በጨዋታው የማይሰለፉ ሲሆን ከኮት ዲ ኦር ጋር በተደረገው ጨዋታ በጉዳት ከሜዳ የወጣው ሳምሶን ጥላሁን ከጉዳቱ አገግሞ ይሰለፋል ተብሏል፡፡