በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ብቸኛ ጨዋታ ሀዋሳ ከነማ አዳማ ከነማን አስተናግዶ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡
ግብ በመስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት አዳማዎች ሲሆኑ የቀድሞው የሀዋሳ ከነማ አጥቂ ዮናታን ከበደ ግቧን አስቆጥሯል፡፡ የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የተጠናቀቀውም በአዳማ 1-0 መሪነት ነበር፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ተመስገን ተክሌ ሀዋሳን አቻ የምታደርግ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ጨዋታውም 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
የአቻ ውጤቱን ተከትሎ አዳማ አንድ ደረጃ አሻሽሎ 8ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ደግሞ 2 ደረጃዎችን አሻሽሎ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ቅዳሜ በመከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ የተጀመረው የ17ኛው ሳምንት ጨዋታ አርብ ወላይታ ድቻ ከ ደደቢት ሶዶ ላይ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል፡፡