ሲዳማ ቡና ዩጋንዳዊ አጥቂ አስፈረመ

ዩጋንዳዊው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የገብረመድኅን ኃይሌውን ስብስብ ተቀላቅሏል።

በሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ከቀናት በፊት ጋናዊው የመሐል ተከላካይ ያኩቡ መሀመድን በአንድ ዓመት ውል መቀላቀሉ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የክለቡ ሁለተኛ የውጪ ዜጋ ተጫዋች በማድረግ ዩጋንዳዊው አጥቂ ዴሪክ ንሲምባቢን በአንድ ዓመት ውል በዛሬው ዕለት ማስፈረሙን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡

የትውልድ ከተማውን ክለብ ካምፓላ ሲቲን ከለቀቀ በኋላ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ለግብፁ ክለብ ሶሞሀ እየተጫወተ የነበረው ዴሪክ ሲሆን ለሀገሩ ዩጋንዳም የመጫወት ዕድል ያገኘ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ወደ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ በዛሬው ዕለት ለሲዳማ ቡና የአንድ ዓመት ውል ፈርሟል፡፡