ሰበታ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀቀ

ሰበታ ከተማ በዛሬው ዕለት የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር በይፋ አጠናቋል፡፡

አማካዩ ፍፁም ተፈሪ ሰበታን የተቀላቀለ ተጨዋች ሆኗል፡፡ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ደደቢት ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የነበረው ፍፁም የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ከቤተሰብ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ከተለያየ በኋላ ካለ ክለብ ያሳለፈ ሲሆን በሲዳማ ቡና ያሰለጠኑት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ጥሪ ተቀብሎ በይፋ አዲሱ የሰበታ ከተማ ፈራሚ ሆኗል፡፡

ዘላለም ኢሳይያስ ሌላኛው የሰበታ ከተማ አዲስ ፈራሚ ነው፡፡ በደቡብ ፖሊስ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ የእግርኳስ ህይወቱን የመራው አማካዩ ወደ ቀድሞ ክለቡ ደቡብ ፖሊስ ተመልሶ ከተጫወተ በኋላ በ2012 ለሀዋሳ ከተማ በመፈረም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በትውልድ ከተማው ክለብ ከቆየ በኋላ በደቡብ ፖሊስ እና ድሬዳዋ ያሰለጠኑት የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ቡድን ወደሆነው ሰበታ ከተማ አምርቷል፡፡