ወልቂጤ ከተማ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ ሾሟል

ወልቂጤ ከተማ የቀድሞውን የግብ ዘብ አዲሱ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ በማድረግ ቀጥሯል፡፡

ዓምና የክለቡ ግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ የነበሩት በለጠ ወዳጆ ከክለቡ መለየታቸውን ተከትሎ የቀድሞውን አንጋፋ ግብ ጠባቂ ደጉ ደሳለኝ አዲሱ የክለቡ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ መሆናቸው ታውቋል።

የግብ ጠባቂነት ዘመናቸውን በአየር መንገድ የጀመሩት እና በመቀጠል ለኢትዮጵያ መድን ፣ ፊንጫ ስኳር ፣ ሜታ ቢራ ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ያገለገለጀት ደሳለኝ ከክለብ ባሻገር ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድንን ለማገልገል ተመርጠው ነበር፡፡ እግርኳስን ካቆሙ በኋላ ወደ አሠልጣኝነት ህይወት በመግባት በፕሮጀክት ደረጃ ማሰልጠንን የጀመሩ ሲሆን ያለፈውን አንድ ዓመት ደግሞ በአንደኛ ሊጉ ቢሾፍቱ አውቶሞቱቭ ግልጋሎ በመስጠት ካሳለፉ በኋላ አሁን ወደ ወልቂጤ ከተማ አምርቷል፡፡