ብርቱካናማዎቹ ከተከላካያቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል

የድሬዳዋው ተከላካይ ቀሪ የስድስት ወር ውል ቢኖረውም በስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይቷል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በርካታ ዓመታት ከተጫወቱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ሁለገብ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ያሬድ ዘውድነህ ከክለቡ ድሬዳዋ ከተማ ጋር የስድስት ወር ውል ቢኖረውም በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል።

ያሬድ ዘውድነህ ለድሬድዋ ከነማ በተለያዩ ጊዜያት ለዘጠኝ ዓመታት የተጫወተ ሲሆን ክለቡንም በአንበል ሲያገለግል ነበር። በመሃልም ለዳሽን ፣ወልዲያ እና ጅማ በመፈረም በሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ እርከን ተጫውቶ አሳልፏል።