መከላከያ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አስፈረመ

ወጣቱ የፊት መስመር ተጫዋች ወደ መከላከያ አምርቷል፡፡

በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ መሪነት በቢሾፍቱ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በማገባደድ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው መከላከያ ወጣቱ የፊት መስመር አጥቂ ብሩክ ሰሙን በአንድ ዓመት ውል የግሉ አድርጓል፡፡

ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር በወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አብሮ መስራት የቻለው አጥቂው የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊጉ አቃቂ ቃሊቲ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን የቀድሞው አሰልጣኙ ዮሀንስ ሳህሌን ጥሪ በመቀበል በይፋ ወደ ጦሩ አምርቷል፡፡