ዋልያዎቹ የመጨረሻ ልምምዳቸውን አድርገዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ነገ ከሌሶቶ ጋር ለሚያደርገው የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ዛሬ ጠዋት የመጨረሻ ልምምዱን አድርጓል፡፡

በዛሬው የልምምድ ፕሮግራም ላይ ግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰው እና አማካዩ ኤፍሬም አሻሞ በጉዳት ልምምድ ያልሰሩ ሲሆን ለነገው ጨዋታም እንደማይደርሱ ተነግሯል፡፡

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ እና ረዳቶቻቸው በዛሬው ልምምድ ላይ መሰረታዊ ቴክኒክ ላይ ያተኮሩ ሲሆን የመከላከል እና የማጥቃት ፣ የቦታ አያያዝ ፣ የቅብብል እና የቆሙ ኳሶች አጠቃቀም ላይ ልምምድ አድርገዋል፡፡

የሌሶቶ ብሄራዊ ቡድን በሆምላንድ ሆቴል አርፎ የእሁዱን ጨዋታ በመጠባበቅ ላይ ሲሆን ዛሬ 10 ሰአት ላይ በባህርዳር ስታድየም ልምምዱን ያደርጋል፡፡ የሌሶቶ ብሄራዊ ቡድን ልምምድ በሚያደርግበት ሰአት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋዜጣዊ መግለጫ በግራንድ ሆቴል እና ስፓ ይካሄዳል፡፡

 

አብርሃም ገ/ማርያም – ከባህርዳር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *