የከፍተኛ ሊግ ፍጻሜ | ወልዋሎ ዓ.ዩ. ከ ጅማ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT   ወልዋሎ  0-1  ጅማ ከተማ 

-22′ አቅሌስያስ ግርማ (ፍቅም)


ተጠናቀቀ!!!

የ2009 የኢትዮዽያ ከፍተኛ ሊግ በጅማ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ 
ተጨማሪ ደቂቃ – 3

የተጨዋች ለውጥ – ጅማ ከተማ
85′ ኄኖክ መሀሪ ወጥቶ ኢብራሂም ከድር ገብቷል።

82′ ወልዋሎዎች በግምት ከ27 ሜትር ርቀት ያገኙትን ቅጣት ምት ሳይጠቀሙበት ቀርተው በመልሶ ማጥቃት አቅሌሲያ ግርማ ያገኘውን ግልፅ የግብ አጋጣሚ አመከነ፡፡

71′ ሁለቱም ቡድኖች በጨዋታው ምንም አይነት የተደራጀ አጨዋወት እያሳዩን አይገኙም።

የተጨዋች ለውጥ – ወልዋሎ
57′ ከድር ሳህለ ገብቶ ቴድሮስ መንገሻ ወጥቷል፡፡

55′ ይህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ የጎል ሙከራ ባናአይበትም በጨዋታው ጠንካራ የመሸናነፍ ፉክክር እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

ተጀመረ!

ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

እረፍት!

የመጀመርያው አጋማሽ በጅማ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

40′ ወልዋሎዎች ጎሉ ከተቆጠረባቸው ጀምሮ ተጭነው በመጫወት ወደ ጨዋታው የሚመልሳቸውን ጎል ፍለጋ እያጠቁ ይገኛሉ።

33′ ጨዋታው በተደጋጋሚ በሚሰራ ጥፋት ምክንያት እየተቆራረጠ ይገኛል፡፡ የጨዋታውን የመጀመርያ ቢጫ ጅማ ከተማ ሮቤል አስራት ተመልክቷል ።

24′ እንዳለ ከበደ ከሳጥን ውጭ አክርሮ የመታው ኳስ ተጨርፎ ለጥቂት ወጣበት፡፡

ጎልልል!!! ጅማ ከተማ!!!
22′ አቅሌስያስ ግርማ ላይ በተሰራ ጥፋት የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ራሱ አቅሌስያስ መትቶ አስቆጥሯል፡፡

19′ ጨዋታው በሁለቱም በኩል ጥሩ የኳስ ፍሰት ቢታይበትም ወደ ሶስተኛው የሜዳ ክፍል ሲደርሱ የማጥቃት እንቅስቃሴያቸው እየተበላሸ ይገኛል፡፡

13′ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ሳምሶን ተካ በግንባሩ በመግጨት ሞክሮ ለጥቂት በግቡ አግድም ወጥቶበታል።

10′ ጅማዎች በፍጥነት ወደ ጎል በመድረስ ተጭነው እየተጫወቱ ቢሆንም ያገኙትን የግብ አጋጣሚ ግን እየተጠቀሙ አይደለም።

3′ የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራ!
ጅማ ከተማ በኄኖክ መሀሪ አማካኝነት ሞክሮ ግብ ጠባቂው በረከት አማረ አዳነበት። ጅማዎች በዚህ ደቂቃ ውስጥ ተጨማሪ ሙከራ በአቅሌሲያ ግርማ አማካኝነትም ሞክረው ነበር።

ተጀመረ!
የከፍተኛ ሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ተጀምሯል፡፡

10:10 የዕለቱ የክብር እንግዶች ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ የጨዋታው መክፈቻ የኢትዮዽያ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል።

10:07 በዕለቱ የጨዋታው ኮሚሽነር እየተመሩ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ በመግባት ከዕለቱ የክብር እንግዶች ጋር በመተዋወቅ ላይ ይገኛሉ ።

10:04 የጅማ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የጅማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከ40 ቀናት በፊት በድንገተኛ ሞት ባጣነው አሰግድ ተስፋዬ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ በባነር ላይ የተጻፈ ጽሁፍ ይዘው ገብተዋል፡፡

09:55 ሁለቱም ቡድኖች ማሟሟቂያቸውን አጠናቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል ።

የወልዋሎ አዲግራት ዮኒቨርስቲ አሰላለፍ

79 በረከት አማረ ፣11 እዮብ ታደሰ፣ 2 አሳሪ አልመሀዲ፣ 15 ሳምሶን ተካ 8 ግርማ ፅጌ፣ 20 ኤፍሬም ጌታቸው፣ 18 መኩሪያ ደሱ፣ 9 እንዳለ ከበደ፣ 7 አብዱአለም አማን፣ 24 አፈወርቅ ሃይሉ፣ 4 ቴዎድሮስ መንገሻ

ተጠባባቂዎች
99 የማነ ገ/ስላሴ ፣ 10 አብርሃ ተዓረ፣ 19 ኤፍሬም ሀ/ማሪያም ፣ 13 አማኑኤል ዘረኡ፣ 16 አለምአንተ ኳስ፣ 12 ከድር ስለህ፣ 11 እዮብ ታደሠ፣ 6 ብርሃኑ አሻም

የጅማ ከተማ አሰላለፍ
1ቢኒያም ታከለ ፣14 ኤሊያስ አታሮ ፣27ሳሙኤል አሸብር፣ 3ሮቤል አስራት ፣2ንጋቱ ገ/ስላሴ ፣22መጣባቸው ሙሉ ፣23አስራት ቱንጆ ፣24አቅሌሲያ ግርማ ፣9ሄኖክ መሃሪ፣ 20 ብሩክ ተሾመ፣

ተጠባባቂዎች
31 መኳንንት አሸናፊ ፣4ጌትነት ታፈሰ፣ 8ሰለሞን ወ/ዳዊት፣16ሮባ ወርቁ፣ ፣6 አብዱልከሪም አባፎጌ ፣ 13 ዝናቡ ባፋ፣ 10 ኢብራሂም ከድር፣ ተዘራ አቡቲ

09:40 የ2009 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የፍፃሜ ተጋጣሚዎች ወደ ሜዳ በመግባት የማፍታቻ ልምምዳቸውን እየሰሩ ይገኛሉ ።

ዳኞች
ዋና ዳኛ – ዘካርያስ ግርማ
ረዳቶች – ትግል ግዛው እና በላቸው ለማ
ኮሚሽነር – ወርቁ ዘውዴ

ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን!

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የፍጻሜ  ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከጅማ ከተማ ይፋለማሉ፡፡ ይህንን የከፍተኛ ሊግ የመዝጊያ ጨዋታም ዳንኤል መስፍን ከስፍራው እያንዳንዷን ክስተት በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ ያደርሳል፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *