ያስር ሙገርዋ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል

ወላይታ ድቻ በዝውውር መስኮቱ ተጫዋቾች ቢለቁበትም አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ክለቡን እያጠናከረ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለትም ዩጋንዳዊው ያስር ሙገርዋን ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡

በወላይታ ለአንድ አመት ለመጫወት የተስማማው ያስር ሐምሌ 25 የውጪ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሲከፈት ለክለቡ በይፋ እንደሚፈርም ታውቋል፡፡

ኦርላንዶ ፓያሬትስን ለቆ ቅዱሰ ጊዮርጊስን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የተቀላቀለ ሲሆን በክለቡ መደበኛ ተሰላፊ ባይሆንም በርካታ ጨዋታዎች ማድረግ ችሏል፡፡ በቀጣዩ አመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋነጫ የሚካፈለው ድቻ ከዚህ ቀደም 5 ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ወደ ድሬዳዋ ለማምራት ተስማምቾ የነበረው አናጋው ባደግ በክለቡ ለተጨማሪ አመታት መፈረሙ ተነግሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ድንቅ የውድድር አመት ያሳለፈውና ለእረፍት በትውልድ ሀገሩ ቶጎ የሚገኘው አራፋት ጃኮ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ለድቻ እንደሚፈርም ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *