ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለት ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል

በዝውውር መስኮቱ ቀደም ብሎ ሁለት ተጫዋቾችን ያስፈረመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ታውቋል፡፡

በጅማ አባ ቡና በውሰት ከውድድር ዘመኑ አጋማሽ ጀምሮ የቆየውና ምርጥ አቋሙን ያሳየው ኄኖክ ካሳሁን ከአዳማ ከተማ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል፡፡ የቀድሞው የደደቢት አማካይ ክለቡን የለቀቀው አሸናፊ ሽብሩን ክፍተት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሞገስ ታደሰ ሌላው ለቡድኑ የፈረመ ተጫዋች ነው፡፡ ሲዳማ ቡናን ለቆ ያለፉትን ሁለት አመታት በአዳማ ከተማ ያሳለፈው ሞገስ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለማምራት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ሳይፈርም ቀርቶ ወደ ኤሌክትሪክ አምርቷል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በተከላካይ መስመር ላይ እጥረት የነበረበት ኤሌክትሪክ በሁለገቡ ተከላካይ አማራጩን ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኤሌክትሪክ ሁለቱ ተጫዋቾችን ከማስፈረሙ በፊት ጥላሁን ወልዴ እና ዮሀንስ በዛብህን ያስፈረመ ሲሆን አሸናፊ ሽብሩ ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ አሳልፈው መኮንን እና ኢብራሂም ፎፋና ከክለቡ የለቀቁ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *