​አዳማ ከተማ አንዳርጋቸው ይላቅን አስፈረመ

ለ3ኛ ተከታታይ አመት ፕሪምየር ሊጉን በ3ኛ ደረጃነት ማጠናቀቅ ያልቻለው አዳማ ከተማ የአንዳርጋቸው ይላቅን ፊርማ አጠናቋል፡፡

በ2007 የውድድር አመት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን ያደገው የቀኝ መስመር ተከላካዩ አንዳርጋቸው በክለቡ እምብዛም የመሰለፍ እድል ሳያገኝ ኮንትራቱን አጠናቆ አዳማ ከተማን በ2 አመታት ውል መቀላቀል ችሏል፡፡ አዳማ በቦታው የሚጫወቱት እሸቱ መና ወደ ወላይታ ድቻ ፣ ሞገስ ታደሰ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማቅናታቸው ቦታውን ለመሸፈን የሚረዳ ዝውውር አድርገዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ዩጋንዳዊው ክሪዚስቶም ንታንቢ ፣ አላዛር ፋሲካ እና ዳንኤል ተሾመን ያስፈረመ ሲሆን ተጨማሪ ተጫዋቾችንም ለማስፈረም ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከደቡብ ሱዳን እና ጋና የመጡ ተጫዋቾች በዚህ ሳምንት በክለቡ የሙከራ ጊዜ አሳልፈው አጥጋቢ አንቅስቃሴ ካሳዩ ለክለቡ የሚፈርሙ ሲሆን የቀድሞው የአዳማ ተስፋ ቡድን አማካይ ከነአን ማርክነህን ከአዲስ አበባ ከተማ ለማስፈረም ድርድር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ከነአን በአአ ከተማ የአንድ አመት ውል ይቀረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *