​ወልዋሎ ሮቤል ግርማን አስፈረመ

ከፍተኛ ሊጉን በ2ኝነት አጠናቆ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለመጀመርያ ጊዜ ያደገው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሮቤል ግርማን አስፈርሟል፡፡

ሮቤል የተጠናቀቀውን የውድድር አመት በድሬዳዋ ከተማ ጀምሮ አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጭር ኮንትራት አምርቶ የነበረ ሲሆን የቀጣይ አመት ማረፊያውን የአዲግራቱ ክለብ አድርጓል፡፡

ክለቡ በዝውውር መስኮቱ ተጨማሪ ተጫዋቾች ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የኤሌክትሪክ ውሉን ያገባደደው ዋለልኝ ገብሬ ክለቡን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ታውቋል፡፡ በነገው እለትም ፊርማውን እንደሚያኖር ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ወልዋሎ የውጪ ተጫዋቾችን ለማምጣት እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *