ኢትዮጵያ ቡና ድንቅነህ ከበደን አስፈረመ

የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች በአኖደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ከተመለከቷቸውና ለማስፈረም ፍላጎት ካሳደሩባቸው ተጫዋቾች መካከል ድንቅነህ ከበደን አስፈርመዋል፡፡

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ድንቅነህ ሀምበሪቾ የአንደኛ ሊግ ምድብ ‘ሠ’ ን በሁለተኛነት እንዲሁም የማጠቃለያ ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቆ ወደ ከፍተኛ ሊጉ እንዲያድግ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ግንባር ቀደሙ ሲሆን በማጠቃለያ ውድድሩ በሚያስቆጥራቸው ወሳኝ ጎሎች እና ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ የፖፓዲችን ቀልብ ስቦ ቆይቶ በመጨረሻም ኢትዮጵያ ቡናን በ3 አመት ውል ተቀላቅሏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከድንቅነህ በተጨማሪ ሌላውን የቡድኑ አጥቂ ቢንያም ጌታቸው ለማግኘት ከጫፍ መድረሱ ታውቋል፡፡ ቢንያም ከስልጤ ወራቤ በውሰት ሀምበሪቾን ተቀላቅሎ ድንቅ አመት ማሳለፍ የቻለ ሲሆን ከወራቤ መልቀቂያ እንዳገኘ ለቡና ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከዚህ ቀደም አለማየሁ ሙለታ ፣ ቶማስ ስምረቱ እና ወንድወሰን አሸናፊን ማስፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *