መቐለ ከተማ 3 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ  

መቐለ ከተማ በክረምቱ የሚያደርገውን የዝውውር እንቅስቃሴ በማጠናከር ሶስት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ ሙሉጌታ ረጋሳ ፣ አለምነህ ግርማ እና ዮሴፍ ድንገቱ ለመቐለ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዮሴፍ ድንገቱ በወላይታ ድቻ 6 የውድድር ዘመናትን ማሳለፍ የቻለ ተጫዋች ሲሆን ክለቡ ከብሔራዊ ሊግ ጀምሮ ባሉት አመታት ባደረገው ጉዞ ከሚጠቀሱ ቁልፍ ተጫዋቾች አንዱ ነበር፡፡

የግራ መስመር ተከላካይ የሆነው አለምነህ ግርማ በ2007 ክረምት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ኢትየዮ ኤሌክትሪክን ከተቀላቀለ በኋላ ወጣ ገባ በሆነ ሁኔታ የመሰለፍ እድል አግኝቷል፡፡

ሌላው ለክለቡ የፈረመው የመስመር አጥቂው ሙሉጌታ ረጋሳ ነው፡፡ ወልዲያ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ አስተዋፅኦ ካደረጉ ተጫዋቾች መሀል የሚጠቀስ ተጫዋች ነው፡፡

መቐለ ከተማ በዝውውር መስኮቱ በስፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን እስካሁንም ሶስቱን ተጫዋቾች ጨምሮ 10 አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *