በወዳጅነት ጨዋታ ዛምቢያ ኢትዮጵያን ዛሬ ከሰዓት ታስተናግዳለች  

በቀጣዩ ሳምንት ኬንያ በመጪው ዓመት ለምታስተናግደው በአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና (ቻን) ውድድር ለማለፍ በሚደረገው የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎች እንዲረዳቸው ዛምቢያ እና ኢትዮጵያ በአቋም መለኪያ ጨዋታ ዛሬ ከሰዓት ሉሳካ ላይ ይገናኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሐሙስ ወደ ሉሳካ ያቀና ሲሆን በሰንሴት ስታዲየም ቀለል ያሉ ልምምዶችን ማድረግ ችሏል፡፡

ውድላንድስ ስታዲየም ላይ በሚደረገው ጨዋታ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ለዛምቢያ እግርኳስ ማህበር (ፋዝ) ድህረ-ገፅ በሰጡት አስተያየት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሁለቱን ቡድኖች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው፡፡ “ይህ ጨዋታ ለሁለታችንም ወሳኝ ነው፡፡ ዛምቢያ ከእኛ የተሻለ ቡድን ነው ስለዚህም ከጨዋታው እንማራለን፡፡ “
የዛምቢያ አሰልጣኝ ዌድሰን ናይሬንዳ በበኩላቸው ቺፖሎፖሎዎች በመሻሻል ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ “ጨዋታው ሰዎች ከተመለከቱት የስዋዚላንዱ ጨዋታ የተሻለ እንደሚሆን እንጠብቃለን፡፡ መልካሙ ነገር በሚመጡት ጨዋታዎች እየተሻሻልን ለመሄድ መሞከራችን ነው፡፡ ቡድናችን ለረጅም ግዜ አብሮ በቆየ ቁጥር እየተጠናከረ ነው የመጣው፡፡”

ሁለቱም ሃገራት በመጀመሪያው የማጣሪያ ዙር ተጋጣሚዎቻቸውን ያለምንም ችግር ማሸነፍ ቢችሉም በመጨረሻ ማጣሪያ ከጠንካራ ሃገራት ጋር ተፋጠዋል፡፡ ዛምቢያ ስዋዚላንድ ላይ የግብ ናዳ አዝንባ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ስትገናኝ ጅቡቲን ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ሱዳንን በቀጣዮ ሳምንት ታስተናግዳለች፡፡ የአቋም መለኪያ ጨዋታው ዛሬ ከሰዓት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡ በተያያዘ የኢትዮጵያ ተጋጣሚ ሱዳን በመጪው ሰኞ ኪጋሊ ላይ ከሩዋንዳ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ስፍራው አርብ ምሽት አምርታለች፡፡ ልክ እንደሱዳን ሁሉ ሩዋንዳ በቻን ማጣሪያ በቀጣዩ ሳምንት ከዩጋንዳ ጋር ላለባት ጨዋታ የሰኞው የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደሚረዳት ጠብቃለች፡፡

ወደ ሉሳካ የተጓዘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው እና ሳምሶን አሰፋ ( ሁለቱም ከድሬዳዋ ከተማ) ፣ ለአለም ብርሃኑ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

ተከላካዮች

አብዱልከሪም መሃመድ፣ አስቻለው ታመነ (ሁለቱም ከቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አንተነህ ተስፋዬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከተማ)፣ ደስታ ዮሃንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ተስፋዬ በቀለ (አዳማ ከተማ)

አማካዮች

ምንተስኖት አዳነ፣ ሙሉአለም መስፍን፣ ጋዲሳ መብራቴ (ሶስቱም ከቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ታፈሰ ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ)፣ ብሩክ ቃልቦሬ

አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ (ደደቢት)፣ አብዱልራህማን ሙባረክ (ፋሲል ከተማ)፣ ሳሙኤል ሳሊሶ (መከላከያ)፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)

የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች

ቶስተር ንሳባታ (ዛናኮ)፣ አለን ቺብዊ (ፓወር ዳይናሞስ)፣ ኬልቨን ማሉንጋ (ናካና)

ተከላካዮች

ዶናሻና ማላማ፣ ሞሰስ ንዮንዶ፣ ባስተን ሙቺንዱ (ሶስቱም ከናካና)፣ ፋክሰን ካፑምቡ፣ ሳይመን ሲልዊምባ (ሁለቱም ከዜስኮ ዩናይትድ) ዛየን ቴምቦ (ዛናኮ)፣ አይዛክ ሳሙጆንፓ (ፓወር ዳይናሞስ)፣ አድሪያን ቻማ (ግሪን ቡፋሎስ)፣ ዌብስተር ሙሌንጋ (ሬድ አሮውስ)

አማካዮች

ኮንዳዋኒ ምቶንጋ፣ ጆን ቺንጋንኡ (ሁለቱም ከዜስኮ ዩናይትድ)፣ ጃክ ቺርዋ፣ ማይክ ካቲባ (ግሪን ቡፋሎስ)፣ ጎድፍሬ ንግዌንያ (ፓወር ዳይናሞስ)፣ ኮሊንስ ሲኮምብ (ናፕሳ ስታርስ)፣ አውገስቲን ሙሌንጌ፣ ኤርነስት ምብዌ (ሁለቱም ዛናኮ)፣ ሉቢንዳ ሙንዲያ (ሬድ አሮውስ)

አጥቂዎች

ማርቲን ፒሪ (ፓወር ዳይናሞስ)፣ ጀስቲን ሶንጋ (ንካዋዚ)

የፊት መስመር ተሰላፊው ብሪያን ምዊላ ወደ ደቡብ አፍሪካው ፕላቲኒየም ስታርስ ያደረገውን ዝውውር ተከትሎ ከቡድኑ ውጪ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *