ኢትዮጵያ ከ ሱዳን – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

  FT   ኢትዮጵያ  1-1  ሱዳን 

76′ ሰይፈዲን መኪ ባኪት | 83′ አብዱራህማን ሙባረክ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ የመልሲ ጨዋታ ከ1 ሳምንት በኋላ በሱዳን ይካሄዳል፡፡

ቢጫ ካርድ
90+2′
አክራም አልሃዲ ሳሊም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 3

የተጫዋች ለውጥ – ሱዳን
88′
መሃምድ ኦስማን ወጥቶ አልጣሂር ባኪር ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
85′
ጋዲሳ መብራቴ ወጥቶ ሳሙኤል ሳሊሶ ገብቷል፡፡ ይህ ጨዋታ ለሳሙኤል የመጀመርያው ኢንተርናሽናል ጨዋታው ነው፡፡

ጎልልል!!!! ኢትዮጵያ
በመልሶ ማጥቃት የመጣውን ኳስ ጌታነህ አሻግሮለት አብዱራህማን ሙባረክ በአግባቡ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን አቻ አደረገ፡፡ ለአብዱራህማን የመጀመርያ ኢንተርናሽናል ግብ ሆናለች፡፡

81′ ዋለልዲን ከድር በሳጥኑ የቀኝ ክፍል የሞከረው አደገኛ ኳስ የግቡ አግዳሚ ለትሞ ወጥቷል፡፡

ጎልልል!!! ሱዳን

76′ ሰይፈዲን መኪ በራሱ ጥረት ወደ ሳጥን ይዞ በመግባት ሱዳንን መሪ የምታደርግ ጎል አስቆጠረ፡፡ 0-1

75′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ማጥቃት ወረዳው ሲደርሱ ደካማ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ቢጫ ካርድ
71′
ብሩክ ቃልቦሬ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሱዳን
69′
ኤልሳማኒ ኤልሳዊ ገብቶ ማዝ አብዱራህማን ወጥቷል

58′ ያለፉት ጥቂት ደቂቃዎች እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ የሜዳ አጋማሽ ላይ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሱዳኖች በተደጋጋሚ ሙከራ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ፡፡

57′ ሰይፈዲን መኪ የሞከረውን አደገኛ ኳስ ጀማል ጣሰው እንደምንም አውጥቶበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
53′
ነስረዲን አብደላ በአዲስ ግደይ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

50′ ዋሊኤልዲን ከድር የኢትዮጵያ ተከላካዮች የፈጠሩት የትኩረት ማጣት ችግር አይቶ ያቀበለውን ኳስ ሰይፈዲን መኪ ከጀማል ጣሰው ጋር አንድ ለአንድ ቢገናኝም አምክኖታል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡

የሁለተኛ አጋማሽ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ

– ብሩክ ቃልቦሬ ገብቶ ታፈሰ ሰለምን ወጥቷል፡፡
– ምንተስኖት አዳነ ገብቶ አብዱልከሪም አህመድ ወጥቷል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

35′ ከመሀል ሜዳ በረጅሙ የተሻገረውን ኳስ አዲስ ግደይ ሞክሮ ሲመለስ ደስታ ጥሩ አጋጣሚ ቢያገኝም ምቱ ጠንካራ ባለመሆኑ ግብ ጠባቂው በቀላሉ ይዞታል፡፡

33′ በግምት 25 ሜትር የተገኘውን ቅጣት ምት ጌታነህ መትቶ ግብ ጠባቂው ኢክራም አድኖበታል፡፡

30′ ጨዋታው ወጥ አልባ እንቅስቃሴ እየተካሄደበት ይገኛል፡ 

26′ አቡ አጋላ በመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ከመሀል ሜዳ እየገፋ ወደ ሳጥን ገብቶ የሰጠውን ኳስ ሰይፈዲን ማኪ ወደ ግብ መትቶ ወደ ውጭ ወጥታለች፡፡ የሱዳን ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ሙከራም ሆናለች

20′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማጥቃት እንቅስቃሴ የተሻለ ሲሆን የሱዳን ብሔራዊ ቡድን በመጠኑ በመከላከል ተጠምደው ታይተዋል፡፡

19′ አቡ አጋላ በራሱ ግብ ክልል በሰራው ስህተት ጌታነህ ከበደ ነጥቆት ወደ ግብ ቢመታም የቀኝ ቋሚውን ታካ ወጥታለች፡፡

18′ አዲስ ግደይ ለጌታነህ ከበደ መሀል ለመሀል አሾልኮ የሰጠውን ኳስ የሱዳኑ ግብ ጠባቂ ኢክራም አልመሀዲ ቀድሞ ይዞበታል፡፡

13′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተደጋጋሚ ወደ ሱዳን ግብ ክልል ቢደርስም የተከላካይ መስመሩን አስከፍቶ መግባት አልቻለም፡፡

ተጀመረ!

ጨዋታው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የኢትዮጵያ አሰላለፍ

12 ጀማል ጣሰው – 2 አብዱልከሪም መሐመድ – 3 ደስታ ዮሀንስ – 4 አንተነህ ተስፋዬ – 15 አስቻለው ታመነ – 6 ሙሉአለም መስፍን – 13 ታፈሰ ሰለሞን – 10 አዲስ ግደይ – 11 ጋዲሳ መብራቴ – 18 አብዱራህማን መሐመድ – 9 ጌታነህ ከበደ

ተጠባባቂዎች
23 ለአለም ብርሀኑ
16 ተስፋዬ በቀለ
5 ተካልኝ ደጀኔ
17 ምንተስኖት አዳነ
8 ብሩክ ቃልቦሬ
7 ሳሙኤል ሳሊሶ

የሱዳን አሰላለፍ

16. አክራም አልሃዲ ሳሊም – 10. መሃምድ ጣሂር ኦስማን – 2. አቡአግላ አብደላ – 5. ባክሪ በሽር ባክሪ – 6. ሀምዛ ዳውድ ዛካሪያ – 7. ዋለልዲን ከድር ዳያን – 9. ሰይፈዲን ማኪ ባኪት – 11. ማአዝ አብድርሀማን ገሳላ – 18. አብዱርሃማን ኢስሃግ – 13. መሀመድ ሃጋር አሊ – 17. ናስርለዲን አብደላ

ተጠባባቂዎች

1. አውደልካሪም ቶቶ
3. ካታብ ፋይሰል አብደላ
4. ኤልሳማኒ ኤልሳዊ ሰዓድ
8. መሃመድ አብደልራህማን የሱፍ
12. አምጀድ እስማኤል አህመድ
14. ሞፋድል መሃመድ ሃሰን
15. አጣሂር አልጣሂር ባኪር

9:58 የሁለቱም ብሔራዊ ቡድን ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል፡፡

9:55 የእለቱ የክብር እንግዶችም አቶ ጁነይዲ ባሻ ፣ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና የሱዳን የፌድሬሽን ሀላፊወች ተጫዋቾችን እየተዋወቁ ይገኛል፡፡

9:50 የሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ተጫዋቾች እና ዳኞች ከመልበሻ ወጥተው ወደ ሜዳ እየገቡ ይገኛሉ፡፡

9:40 በስታድየሙ ውስጥ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ባሻገር መጠነኛ የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ተገኝተዋል፡፡

9:10 የሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛሉ፡፡ 

ሰላም!

በቻን ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ሰዳንን ልክ 10:00 ሲል ታስተናግዳለች፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም ጨዋታውን ከሀዋሳ ስታድየም በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ ታደርሳለች፡፡

መልካም ቆይታ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *