የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኮከቦች ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

ነሐሴ 27 ቀን 2009 ሊደረግ ታስቦ የነበረው የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2009 የውድድር ዘመን የኮከቦች ምርጫ ላልተወሰነ ቀን መራዘሙ ታውቋል።

የ2009 የውድድር ዘመን ቀድሞ ከነበረው የኮከቦች ምርጫ በተለየ ሁኔታ አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ለማዘጋጀት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ጀምሮ የነበረው የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እሁድ ነሐሴ 27 ቀን የኮከቦችን ምርጫ እንደሚያደርግ ቢነገርም ፕሮግራሙ በተለያዩ ምክንያቶች እንደተራዘመ ለማወቅ ችለናል። ለፕሮግራሙ መራዘም እንደምክንያት የቀረበው ከኢትዮዽያ ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬሽን (EBC) ጋር የተፈጠረው አለመግባባት እልባት ባለማግኘቱ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል።

ፌዴሬሽኑ የኮከቦች ምርጫውን ላልተወሰነ ቀን ከመራዘሙ ውጪ መቼ እና የት እንደሚደረግ ግን አላስታወቀም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *