የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ክለብ የመቀጠል ፈንታ አለየለትም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር ለ18 አመታት ከቆየበት የሀገሪቱ ትልቁ ሊግ በ2009 የውድድር ዘመን መውረዱን ተከትሎ እንደ ክለብ የመቀጠል እጣፈንታው አለየለትም፡፡

ክለቡ በከፍተኛው ሊግ እንደመወዳደሩ በተጫዋች ግዢ እና የቀጣይ አመት ዝግጅት ዙርያ እስካሁን ዝምታን የመረጠ ሲሆን ክለቡ በከፍተኛ ሊጉ ለመሳተፍ ፍላጎቱ መቀዛቀዙና የሴቶች ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች ወደ ሌሎች ክለቦች እያመሩ መሆኑ ባንኩ የስፖርት ማህበሩን ለማፍረስ ሳይዘጋጅ አይቀርም እየተባለ ከክለቡ አካባቢ እየተሰማ ይገኛል፡፡

የስፖርት ማህበሩ በክለቡ ቀጣይ እጣ ፈንታ ላይ ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን ዝርዝር ጉዳዩን ከጋዜጣዊ መግለጫው በኋላ የምንመለስበት ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *