አርባምንጭ ከነማ ከአሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ ጋር ሊለያይ ተቃርቧል

 

አርባምንጭ ከነማን ለረጅም ጊዜ ያሰለጠኑት አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ ክለቡን ለቀው ወደ ሲዳማ ቡና ሊያመሩ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

በ2004 ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደገ ወዲህ ቡድኑን በአሰልጣኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት አሰልጣኝ አባይነህ በሲዳማ ቡና የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ምክትል ሊሆኑ ተቃርበዋል ተብሏል፡፡

አርባምንጭ በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ወሳኞቹ ተጫዋቾቹን አጥቷል፡፡ ሙሉአለም መስፍን እና አንተነህ ተስፋዬ ወደ ሲዳማ ቡና ያመሩ ሲሆን የይርጋለሙ ክለብ ሁለቱን ተጫዋቾች ለ2 አመት ለእያንዳንዳቸው 1.1 ሚልዮን ብር በመክፈል አስፈርሟቸዋል፡፡ አሁን ደግሞ ከቡድኑ ጋር መስማማት ያልቻሉትን አለማየሁ አርባምንጭን ለቀው ወደ ሲዳማ ለማምራት ተስማምተዋል ተብሏል፡፡

ሌሎች የሊጉ ክለቦች በዝውውር እንቅስቃሴው በስፋት እየተሳተፉ ቢሆንም አርባንጭ ከነማ ግን የተጫዋቾችን ኮንትራት በማራዘም እና በመጪው ሐምሌ 24 በሚጀመረው የብሄራዊ ሊግ ውድድር ላይ በሚሳተፉ ተጫዋቾች ላይ ትኩረት እንዳደረገ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *